House and Building Sale

ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት የመኖሪያ ቤት የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል

Description

1ኛ የጨረታ ማስታወቂያ

በአፈፃፀም ከሳሽ ሲሳይ ያደቴ እና በአፈፃፀም ተከሳሾች እነ 1ኛ. አስራት ጀንበር 2ኛ እመቤት ስዩም 3ኛ. ሔለን ከተማ ሶስት ሰዎች መካከል ያለውን የፍርድ አፈፃፀም የፍታብሔር ክርክር አስመልክቶ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ምስራቅ ቋሚ ችሎት በቀን 26/01/2018 በዋለው ችሎት የሰጠውን ትዕዛዝ እና በቀን 10/02/2019 በዋለው ችሎት የሰጠውን ትዕዛዝ በድምሩ 03 ገጽ ከዚህ ማስታወቂያ ጋር ልከንላችኋል። ስለዚህ የፍርድ ባለ ዕዳ ንብረት የሆነ ባለ 2 (ሁለት) ፎቅ ህንፃ እና 1 (አንድ) መሬት (ግራውንድ) (B+G+2) የሆነ በአዳማ ከተማ አባ ገዳ ክ/ከተማ በዳቱ ወረዳ መስተዳድር ውስጥ 262.30 ካ.ሜ (ሁለት መቶ ስልሳ ሁለት ነጥብ ሰላሳ ካ.ሜ) የሆነ መሬት ላይ የሚገኝ የካርታ ቁጥሩ 2323/2001 ሆኖ አቶ ኃይሉ ሰብስቤ በተባለ ሰው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ እና ካርታ በተሰጠበት ወቅት አዋሳኞቹ በምስራቅ ዶ/ር አማኑኤል፣ በምዕራብ የመኖሪያ ቤት፣ በሰሜን መንገድ እና በደቡብ መኖሪያ ቤት የሚያዋስኑት በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 7,534,837 (ሰባት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰላሳ አራት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ ሰባት) በቀን 14/03/2019 ጠዋት ከ2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ግልፅ በሆነ ጨረታ ተሸጦ የጨረታው ውጤት በቀን 15/03/2019 ጠዋት 4፡00 ሰዓት እንዲቀርብ ታዟል።

ስለዚህ በጨረታው ላይ ተሳትፋችሁ መግዛት የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሳተፍ ትችላላችሁ።

1ኛ. የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25/100 ፐርሰንት ብር 1,883,709.25 (አንድ ሚሊየን ስምንት መቶ ሰማንያ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠኝ ብር ከ25/100) በስንቄ ባንክ በሲፒኦ ማስያዝ ወይም

2ኛ. በባንክ የተረጋገጠ ቼክ በማቅረብ መመዝገብ ይቻላል።

3ኛ, ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ ጠዋት ከ2፡30 ሰዓት ጀምሮ ቀርባችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ

4ኛ, ይህ ማስታወቂያ ከቀጠሮ ቀን 12/02/2019 ታትሞ ለ30 (ሰላሳ) ቀናት አየር ላይ እንዲውል፣

5ኛ. ይህ ጨረታ የሚከፈተው ሕንፃው በሚገኝበት ቦታ እና በተገለፀው ሰዓት ነው።

6ኛ. ይህንን ማስታወቂያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ እና ከለቻ ኦሮሚያ ጋዜጣ እንዲፈፅሙ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ቋሚ ችሎት አዟል።

ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-23 10:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Oct 24, 2026)
  • Posted at: 2026-10-24T10:01:45.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders