Equipment and Accessories
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ ከንቲባ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በሀዋሳ ከተማ አስ/በመስቀል አደባባይ ውስጥ ለሚከበረው ክብረ በዓል የሚሆን የመድረክ ስቴጅ እና የውጭ እስክሪን ኪራይ ግዥ ጨረታ መሠረት ለማከራየት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ ከንቲባ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በሀዋሳ ከተማ አስ/በመስቀል አደባባይ ውስጥ ለሚከበረው ክብረ በዓል የሚሆን የመድረክ ስቴጅ እና የውጭ እስክሪን ኪራይ ግዥ ጨረታ መሠረት ለማከራየት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መከራየት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅት መካከል አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት;
1. በዘርፉና ተመሳሳይ ሥራ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ፤-
2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
4. በጨረታው እንዲሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
5. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ ፣
6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ( አዲስ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር 200(ሁለት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10(አሥር) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ፤ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
ሀዋሳ
Tender details
- Deadline: 2026-11-03
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10(አሥር) ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-03 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10(አሥር) ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 24, 2026)
- Posted at: 2026-10-24T10:04:49.000Z
- Source: Qelal Tenders