Stationery
በአብክመ ደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02 /2019
በአብክመ ደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ
- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 2. የደንብ ልብስ /ጫማ ፣ የተዘጋጁ ልብሶች እና ብትን ጨርቅ/
- ሎት 3. የእንስሳት መድሀኒት
- ሎት 4. የፅዳት እቃዎች
- ሎት.5 የስፖርት አልባሳት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች ለጨረታ ሲመጡ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ /የግብር ክሊራንስ/ ማቅረብ የሚችሉ
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
4. ከ500000/ከአምስት መቶ ሽህ ብር /በላይ የነጠላ ወይም የጥቅል ግዥ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት ለዚህም የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
5. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛዉ ቀን 11፡30 ድረስ ማግኘት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 ለጽህፈት መሳሪያዎች 20,000 /ሀያ ሽህ ብር/፣ ለሎት 2 የደንብ ልብስ /ጫማ 20,000/ ሀያ ሽህ ብር/፣ለተዘጋጁ ልብሶች 20,000/ ሀያ ሽህ ብር/ ፣ ለብትን ጨርቅ 20,000/ ሀያ ሽህ ብር/ ፤ ለሎት 3 ለእንስሳት መድሀኒት 20,000(ሀያ ሽህ ብር/ ፤ ለሎት 4 ለፅዳት እቃዎች 2,000/ሁለት ሽህ ብር/ ለሎት 5 ስፖርት አልባሳት 10000/አስር ሽህ ብር/በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ ይህም ጨረታ ማስከበሪያው ለ73 / ሰባ ሶስት/ ቀናት መቆየት አለበት።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ን/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ11 ኛዉ ቀን ከረፋዱ እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ በማስገባት ይታሸጋል፡፡ በዚሁ እለት ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅደም ተከተል በስራ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥናን/አስ/ደ/ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል፡፡ 11ኛዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀናት ታሽጎ ይከፈታል።
8. በጨረታው ለመጫረት የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር - 033-450-02-22 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በጨረታው አከፋፈት ሰነ ስርአት ላይ መሳተፍ አለባቸው ግን ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ ከመከፈቱ አይስተጓጎልም።
10. ጨረታ ሰነዱ በነጠላም ሆነ በድምር ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
11. የሞሉትን ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ ድምር ማስቀመጥ አለባቸው።
12. ለደንብ ልብሱ ሳምፕል ስላቀረብን አይቶ መጫረት አለበት።
13. ዉድድሩ የሚካሄደው ከ ሎት 1 እስከ ሎት 5 በየምድቡ በሎት ነዉ።
14. የመጫረቻ ሰነዱ ፀንቶ የሚቆየው ለ45 ቀን ነው።
15. ለአቅርቦት ግዥ ከብር 20000.00(ሀያ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ 3% ዊዝሆልድንግ ታክስ ይከፍላል።
16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቹ ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሀላፊነት አይወስድም።
17. እቃው ገቢ የሚሆነው በመቅደላ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች ንብረት ክፍል ነው።
የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-03
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን ከረፋዱ እስከ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-03 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Mekdela Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 24, 2026)
- Posted at: 2026-10-24T10:12:44.000Z
- Source: Qelal Tenders