Stationery

በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበ በጀት የተለያዩ የጽህፈት፣ የጽዳት እና ከፊል ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ፋ/ኢ/ቢ/ጨ/መ/ቁ 001/2019
የጨረታ ማስታወቂያ

በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበ በጀት የተለያዩ የጽህፈት የጽዳት እና ከፊል ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃወችን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ፡- ቀጥሎ የተዘረዘሩት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የተሠማሩና ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድና ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፣
የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣

  • ተጫራቶች ለተወዳደሩበት ጨረታ አግባብነት ያለው የተሟላ ማስረጃና ሠነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  •  የጨረታውን ሰነድ በድሬደዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ከግዥና ፋይናንስ ንብረት አሰተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 20 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት 9/2/2019 ጀምሮ ለ15ተከታታይ ቀናት ማለትም አየር ላይ የሚውል ስለሆነ በነዚህ ቀናቶች የጨረታ ሰነዱን 300(ሶሰት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፣
  • ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ጥቅምት 24/02/2019ዓ/ም አርብ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዳይሬክቶሬቱ ቢሮ በግልጽ ይከፈታል፡፡
  • ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት ግዥ ብር20,000(ሃያ ሽህ) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ከዋናው ሰነድ ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ የጨረታ ሰነዳቸውን በአንድ በታሸገ ፖስታ የእያንዳንዱን ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  • ያሸነፈው ተጫራች የተጠየቀውን የጽህፈት የጽዳት እና ከፊል ቋሚ እቃወች ግዥ ትዕዛዝ እንደተሰጠው በግዥው ፍላጎት መግለጫው መሰረት
  • በአንድ ሳምንት ውስጥ በድሬደዋ አሰተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ መጥቶ ውል መግባት አለበት፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈበት ዋጋ
  • ውል ማከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና CPO ወይም ያልተገደበ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝና መስጠት የሚችል መሆን አለበት፡፡
  • ተጫራቾች ለተጫረቱት ዝርዝር እቃዎች የጨረታ ስነድ ይዘው ሲመጡ ናሙና የሚጠይቁትን የቢሮ መገልገያ እቃዎች ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኃላ የሚመጣ የጨረታ ዶክመንት ተቀባይነት የለውም፡፡
  • መስሪያ ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘጨረታን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግዎ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፦

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የፋይናንስ ግዥና ንብረት ንብረት አስተዳደር ዳይሮክቶሬት
የስልክ ቁጥር 0915 732 312 ወይንም 0928 118000
ፋክስ ቁጥር 0251-11-77-29
ድሬ ዳዋ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ጥቅምት 24/02/2019 ዓ/ም አርብ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-03 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ጥቅምት 24/02/2019 ዓ/ም አርብ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Dire Dawa Administration Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 300(ሶሰት መቶ ብር ብቻ)
  • Published on: Melekite Dire (Oct 21, 2026)
  • Posted at: 2026-10-24T10:52:24.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders