Vehicle and Machinery Sale

የተሽከርካሪ ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ፌቨን ገረመው እና በፍ/ባለዕዳ  ክንፈ ታደለ መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም  ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍቤት በመ/ቁጥር/ 13204 በ3/10/2018 ዓ.ም. እና  በኮ/መ/ቁ/22654 በ8/11/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ  ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ውስጥ የሚገኝ የሰ/ቁ.ኮድ 3 –B42849 አ.አ. ኮሮላ  ተሸከርካሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1,688,301 ( አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰማንያ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ አንድ) ሆኖ የትራክሽን ታከለ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታይቶ ህዳር 4 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረበ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረቃ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅክፍልድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በፌ / ፍ / ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-13
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-11-13 14:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Oct 25, 2026)
  • Posted at: 2026-10-26T08:14:30.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders