Textile, Garments and Uniforms
ቃሊቲ 2ኛ ደ/ት/ቤት የደንብ ልብሶች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የቢሮ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የጥገና፣ የቧንቧ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የህትመት ስራዎች፣ የተለያዩ የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ መድሀኒቶች እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ቃ/ሁ / ደ/ ት /ቤት ግ/ጨ 001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ ከተማ ቃሊቲ 2ኛ ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት፡-
- የደንብ ልብሶች
- አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
- የቢሮ የፅህፈት መሳሪያዎች
- ቋሚ ዕቃዎች
- የጥገና፣ የቧንቧ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
- የህትመት ስራዎች
- የተለያዩ የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ መድሀኒቶች እና የህክምና
- መገልገያ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያወጡና የተሰጣቸው ንግድ ፈቃድ (አንድ) ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TN No) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በወጣው ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ዘውትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ቢሮ ቁጥር 8 የግዢና ንብረት አስተዳደር ክፍል በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ ለሚገዛቸው ዕቃዎች ማለትም በጨረታ ሰነዱ ላይ በከፍል 6 ላይ የተዘረዘሩትን የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች ዝርዝር መግለጫ ላይ ናሙና ሳምፕል እንድታቀርቡ በተጠየቀው መሠረት የተጠየቁትን ናሙና ሳምፕል) የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ቢሮ ቁጥር 8 የግዥ የስ/ሂደት እንድታስገቡ እየገለጽን ናሙና (ሳምፕል) ያልቀረበባቸው ዕቃዎች ውድቅ እንደሚሆኑባችሁ አውቃችሁ ለምትወዳደሩበት ዕቃዎች በሙሉ ናሙና(ሳምፕል) እንድታቀርቡ እያሳሰብን የምታቀርቡትን ናሙና ሳምፕል በተመለከተ ት/ቤቱ የራሱን ኮድ የሚሰጥ በመሆኑ 21, በምታቀርቡት ናሙና ሳምፕል ላይ የድርጅታችሁን ስም መጻፍ ወይም መለጠፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው። በተጨማሪም ከጽዳት ዕቃዎች በረኪና፣ ዲቶል፣ ከቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎች መካከል እርሳስ፣ እስኪርብቶ፣ ፍሉድ፣ ኡሁ፣ ማርከር እና የማህተም ቀለም የቃሊቲ 2ኛ ደ/ት/ቤት የጥራት ኮሚቴው ዕቃዎቹን ከፍቶ ጥራቱን የሚፈትሽ የሚመረምር መሆኑ እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለሚያቀርቡት/ የላቡራቶሪ መገልገያ፤ ጀነሬተር፤ ላፕቶፕ ሌሎች መሳሪያዎች የሚገልጽ ማንዋል ወይም ዝርዝር መረጃ ከጨረታው ሠነዱ ጋር ተያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት የተከለከለ ሲሆን ነገር ግን ይህ ሆኖ ቢገኝ ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ።
- የጨረታው ዋጋ ለ2 ወር ጸንቶ ይቆያል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሚመለከት አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባችሁ።
- ተጫራቾች በተሰጣቸው የዋጋ መሙያ ሠነድ ላይ ምንም ዓይነት ስፔስፊኬሽን መጨመርም ሆነ መቀነስ አይችሉም።
- ተጫራቾች የወሰዳችሁትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ በሙሉ ሳይገነጣጠል ተመላሽ የምታደርጉ ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሰነድ ት/ቤቱ የማይቀበልና ከውድድር ውጭ የሚያደርግ መሆኑን ይገልጻል።
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ በተጨማሪም ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቶች ከጨረታው ውጭ ሆነው ለወደፊቱም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ፡፡ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረስባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ በመለየትና በፖስታው ላይ በመግለጽ በታሸገ ፓስታ በማድረግ ቃሊቲ 2ኛ ደ/ት/ቤት ግቢ ቢሮ ቁጥር 8 ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቦታ፤ ቀንና ሰዓት በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታ ሳጥኑ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል።
- በጨረታው ላይ ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ እጩ ተወዳዳሪዎች በግምገማው እኩል ውጤት ካቀረቡ ቅድሚያ ለአገር ውስጥ አምራች ለሆኑ ዕድሉን የምንሰጥ ሲሆን አምራች ተወዳዳሪ ካሌለ አሸናፊውን ለመለየት አብላጫ ዕቃዎችን ላሸነፈው እድሉን እንሰጣለን።
- የጨረታ ውጤቱ ይፋ ሆኖ አሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች እንደተለዩ በማስታወቂያ ላይ ከተገለጸ በኋላ ተሸናፊ ተጫራቾች ያሲያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ የይመለስልኝ ደብዳቤ በመጻፍ ተመላሽ ይደረግላቸዋል። አሸናፊ ተጫራች ግን የውል ስምምነት እንዲፈጽም በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ከአሸነፈበት ዕቃ አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 10% የግዢ የውል ማስከበሪያ ሲያሲዙ ቀደም ብለው ያሲያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ 2% ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- ገዢው መ/ቤት በጨረታ ማስታወቂያ የተጠየቀውን ዕቃ ካቀረበው መጠን /ብዛት/ላይ 20% ከውል በፊት የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው!!
- አቅራቢው በገባው የውል ስምምነት መሰረት የዕቃውን ዓይነት፣ መጠን እና ጥራት ጠብቆ በውሉ ላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካላቀረበ የግዢ ፈጻሚ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ በከፍል 8 በልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ በተገለጸው መሠረት አሸናፊ ተጫራች ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 0.01% በየቀኑ ዕቃውን እስከሚያስረክብበት ቀን ድረስ ተቀናሽ ሆኖ ለመስሪያቤቱ የጉዳት ካሳ ገቢ ይሆናል። በተጨማሪም አቅራቢው ያሸነፈበትን ዕቃ ፈጽሞ ካላቀረበ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ 10% መ/ቤቱ ይወርሳል።
- በግዢ ፈጻሚ እና በአቅራቢው መካከል የተለየ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የተያዘው የውል ማስከበሪያ ዋስትና አቅራቢው ግዴታውን ሙሉ በሙሉ እንደተወጣ ሲረጋገጥ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግለታል።
- በጨረታ ሂደቱ ላይ ጉዳት ደርሶብኛል ወይም በጨረታ ግምገማ ውጤት ላይ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በድጋሚ እንዲታይለት የጨረታ ውጤት ይፋ ሆኖ በማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በግዢ ፈጻሚ መ/ቤት የበላይ ኃላፊ በጽሁፍ ቅሬታውን ማቅረብ ይኖርበታል። ሆኖም በተሰጠው ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ሳያቀርብ ቀርቶ ቀነ ገደቡ ካለፈ በኋላ የሚመጣ ቅሬታ ተቀባይነት አይኖረውም።
- በውድድር ወቅት በአንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር በአንዱ ዋጋ መሰረት እና በአሃዝና በፊደል በሚገለጽበት ወቅት ልዩነት ቢኖር በፊደል በተገለጸው መሰረት በማስተካከል ይገመግማል።
- ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙና ሳምፕል/ በሚመረመርበት ወቅት በራሱ ተፈጥሮ ቢጠፋ ወይም ቢበላሸ መ/ቤቱ ካሳ አይከፍልም።
- ያቀረቡት ናሙና የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 60/ስልሳ ተከታታይ ቀናት ውስጥ እንዲወስዱ ተገልጾላቸው ጠይቀው ካልወሰዱ ለመንግስት በውርስ ገቢ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ መጋዘን ድረስ በራሳቸው ትራንስትርት/ወጪ/ በማጓጓዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የሚያቀርቡት የዕቃ አይነት ተገጣጣሚ ከሆነ በራሳቸው ወጪ ገጣጥመው ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ሠነድ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዩች አስመልክቶ ማብራሪያ ቢያስፈልጋችሁ በጽሁፍ ቃሊቲ 2ኛ ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በአካል በመምጣት ማቅረብ /መጠየቅ ትችላላችሁ።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ
|
በሎት 6211 |
54,875.00 ብር |
|
በሎት 6212 |
25,113.00 ብር |
|
በሎት 6213 |
6,000.00 ብር |
|
በሎት 6214 |
3,900.00 ብር |
|
በሎት 6215 |
22,159 ብር |
|
በሎት6218 |
29,060.00 ብር |
|
በሎት 6219 |
9,242.00 ብር |
|
በሎት 6223 |
2,000.00 ብር |
|
በሎት 6313 |
80,000.00 ብር |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
አድራሻ:- አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል
ቤተክርስቲያን እለፍ ብሎ ቸራሊያ ሳይደርስ በስተግራ በኩል 150 ሜትር ያህል ገባ
ብሎ የሚገኘው የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-011 462-6451/+251-011 462-5324/+251-011 439-6550/ 251-439-4857 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ 2ኛደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-04
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-04 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kality Secondary School
- Buyer's registered address: ከቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አለፍ ብሎ ቸራሊያ ሳይደርስ በስተግራ በኩል 150 ሜትር ያህል ገባ ብሎ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 25, 2026)
- Posted at: 2026-10-26T09:28:39.000Z
- Source: Qelal Tenders