Vehicle and Machinery Sale
አንበሳ ባንክ አ.ማ. አውቶሞቢል ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Vehicle and Machinery SaleSales, Disposals and ForeclosureVehicle and Machinery Foreclosure
Addis Ababa
More tags
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
አንበሳ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1147/2012 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሰንጠረዡ ላይ የተጠቀሰውን ንብረት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
የመኪናው ዓይነት፣ የሰሌዳ ቁጥር፣ የሻንሲ ቁጥር እና የሞተር ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
የጨረታ መነሻ የሚከናወንበት ቦታ፤ ቀን እና ሰዓት |
||||
|
የሰሌዳ ቁጥር |
የመኪናው አይነት |
የሞተር ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
የሰራት ዘመን |
||||||
|
1 |
ዲ.ኤ.ቲ አስመጪና ላኪ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር |
ዲ.ኤ.ቲ አስመጪና ላኪ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር |
ሻላ
|
03-B71237 አአ
|
አውቶሞቢል
|
K12MP-4278995
|
MBHCZF63S00165185
|
2021 |
2,400, 000.00 |
ጨረታው የሚከናወነው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህዳር 06 ቀን 2019 ዓም ከቀኑ 8፡00-10:00 ድረስ ይሆናል። |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) ብቻ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አማ ስም በማሰራትና ለጨረታ ማስከበሪያነት በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- የጨረታው ምዝገባ የሚከናወነው ከቀኑ 8፡00 እስከ 9፡30 ድረስ ይሆናል። ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ሲሆን የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሽናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል።
- ጨረታ የሚካሄደው 22 አካባቢ ሌክስ ፕላዛ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይሆናል።
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ከሚያካሂደው የባንኩ የህግ አገልግሎትና ሪከቨሪ ጽቤት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርስው ብቻ አሽናፊ ይባላል።
- የጨረታው አሸናፊ ቀሪውን ገንዘብ አሽናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ (CPO) ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ይከፍላል።
- ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል።
- በሐራጅ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዥ ወይም የነዚህ ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው። ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታዉን ሂደት ለመከታተል በተጠቀሰዉ ቦታ እና ሰዓት እንድትገኙ እያሳሰብን ካልተገኛችሁ በሌላችሁበት ጨረታው የሚከናወን መሆኑን እንገልፃለን።
- ባንካችን ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል።
- ከሚሸጠው ንብረት ጋር የተያያዙ ከጨረታው በፊትም ሆነ በኋላ ማንኛውም ለመንግስት ሊከፈሉ የሚገባቸው ተ.እ.ታን ጨምሮ ማንኛውም አይነት ክፍያዎች፣ ወጪዎች ወይም የግብር ክፍያዎች እንዲሁም በንብረት ማስተላለፍ ሂደት የሚመጡ የአሹራ፤ የእግድ ማንሻ፤ የቦሎ፣ የስም ማዘዋወሪያ ክፍያዎችን ጨምሮ ማንኛውም አይነት ክፍያዎች ወይም ግብር ሙሉ በሙሉ የጨረታ አሸናፊው ገዥው የሚሸፍን ይሆናል።
- ባንኩ ከጨረታ በፊት እና በኋላ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሎም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ ማብራርያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር 011-662-7120 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አንበሳ ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-11-16
- Bid closing time: 16:00
- Bid opening: 2026-11-16 16:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Anbesa Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Oct 25, 2026)
- Posted at: 2026-10-26T12:26:57.000Z
- Source: Qelal Tenders