Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ ቁጥር 1 የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ ቁጥር 1 የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓመት አገልግሎት የሚውል ኦርጅናል አላቂ የቢሮ እቃዎች፤ የፅዳት እቃዎች፤ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፤ የትምህርት እቃዎች፤ ቋሚ እቃዎች፤ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች፤ የህክምና መድኃኒቶችና ህትመቶች ለመግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፤ ቲን-ነምበር እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ይህንኑ የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 እንቁላል ፋብሪካ እምብልታ ሆቴል ከፍ ብሎ ከሚገኘው የጄኔራል ታደሰ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ ጥራት ያለው ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ ናሙና ማቅረብ ባለባቸው ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች እቃዎችን ዝርዝር እና የጨረታ ማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ስማችሁን፣ ፊርማችሁንና አድራሻችሁን ማስፈርና ማህተም በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት በጄኔራል ታደሰ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል።

7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች በሰነድ የሰጡትን ዋጋ መለወጥ ወይም ከውድድሩ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

8. የማወዳደሪያ ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሞላት አለበት።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃዎች ብር 9,500 (ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ) ለሎት 2 የፅዳት እቃዎች ብር 8,500 (ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር) ለሎት 3 የደንብ ልብስ ብር 7,500 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር) ለሎት 4 ቋሚ እቃዎች ብር 6,000 (ስድስት ሺህ ብር) ለሎት 5 የትምህርት እቃዎች ብር 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ለሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ለሎት 7 የህክምና መድኃኒቶች ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ለሎት 8 የተለያዩ ጥገናዎች ብር 7,500 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር) ለሎት 9 የደንብ ልብስ ስፌት ብር 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ለሎት 10 ህትመቶች ብር 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

10. መ/ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ የእቃውን ብዛት እስከ 20% መጨመር ወይም 20% ከውሉ በፊት መቀነስ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።

11. መ/ቤቱ የሚገዛውን እቃ እስከ 6 ወር ዋጋ ጭማሪ ሳይደረግ ተጨማሪ 25% እቃ ግዥ መፈፀም ይችላል።

12. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።

13.ተጫራቹ ያሸነፈውን እቃ የመ/ቤታችን ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት አምጥቶ ማስረከብ አለበት።

14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአገር ውስጥ አቅርቦት ጋር በሚወዳደሩበት ጊዜ 3% ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡ በስልክ ቁጥር 011 827 8952

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ ቁጥር 1 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-04
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-05 10:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: General Tadese Biru No.1 Elementary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Oct 25, 2026)
  • Posted at: 2026-10-26T12:38:22.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders