Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር አሽ/ተሽ/ፍ/ቁ/ባ/ ጉለሌ/ቅ/ጽ/ቤት 2019/001

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፡-

  • ሎት 1. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት 2. የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3. የመኪና ዕቃዎች
  • ሎት 4- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  • ንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ለእያንዳንዱ ሎት ማቅረብ አለባችሁ።
  • ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
  • የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ከአስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 39 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ።

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት፡-

  • ለሎት 1 ፣ 2 ፣ 4 ለእያንዳንዳቸው በተናጥል የ2,000 ብር (ሁለት ሺህ ብር) CPO
  • ለሎት 2 የ1,000 ብር (አንድ ሺ ብር ) CPO ለእያንዳንዳቸው በተናጥል አሠርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
  • ባለሥልጣን መሥሪያ ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲሱ ገበያ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ግቢ ውስጥ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 39

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-154-6606/011-54-61-90 መጠየቅ ይቻላል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-05 10:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Administration Driver and Vehicle Licensing and Control Authority Addis
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 25, 2026)
  • Posted at: 2026-10-26T12:48:19.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders