Equipment and Accessories
ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የICT መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የዕውቅና ፈቃድ አግኝቶ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጀሞ አካባቢ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ ዲግሪ እና በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት ላይ የሚገኝ የትምህርት ተቋም ነው። በመሆኑም ጥራት ያለውን ትምህርት ለመስጠት ግብአት የሚሆኑ የICT መሳሪያዎች ከታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ከአቅራቢ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ለግዥ የተፈለገው የICT መሳሪያዎች
|
No |
Name & Description of Item/Service |
Qty. |
Unit |
Remark |
|
1 |
LCD Projector |
4 |
|
|
|
2 |
Desktop Computer Core i5 16GB RAM and 1TB SSD, Support WIFI |
40 |
|
|
|
3 |
Laptop Corei5 16GB RAM and ITB SSD |
3 |
|
|
ጨረታው ላይ የምትሳተፉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ ጀሞ 1 ለቡ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ድርጅታችን ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር C-116 በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በብር 1,000.00 (አንድ ሺ ብር) መግዛት የምትችሉ ሲሆን ለዚህም ጥሬ ገንዘብ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከቴክኒካል (ህጋዊነት) ዶክመንቱ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አጫራቹ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 74-17-66-00 ወይም 09 74-17-66-17 መደወል ትችላላችሁ
Tender details
- Deadline: 2026-11-04
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ
- Bid opening: 2026-11-04 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hope Enterprise University College
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published on: Reporter (Oct 25, 2026)
- Posted at: 2026-10-26T12:57:15.000Z
- Source: Qelal Tenders