Vehicle and Machinery Sale
ኤልሳቢ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ኤልሳቢ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሰንጠረዡ የተመለከተውን ተሽከርካሪ በአዋጅ ቁጥር 216/92 እና 1147/2019 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
የተበዳሪውና የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
የተሽከርካሪው |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ(ብር) |
|
||||
|
ዐይነት |
የሞተር ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
የተሠራበት ዘመን |
ታርጋ(ሰሌዳ) ቁጥር |
ሐራጁ የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት |
|||
|
ወ/ሪት እየሩሳሌም ፀሃዬ ብርሃኔ |
አዲሱ ገበያ |
ኢትዮ-ሊፋን አውቶሞቢል |
LF479Q3* Y100600343* |
LLV1C2A16 A0006739 |
2010 |
አ.አ3-67423 |
378,763.14(ሶስት መቶ ሰባ ስምንት ሺ ሰባት መቶ ስልሳ ሶስት ብር ከ14/100 ሳንቲም) |
ህዳር 01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እሰከ ጠዋቱ 5፡30 ስዓት |
የጨረታ ደንቦች
1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከተቋሙ በማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በካሽ በመክፈል ከተቋሙ ዋና ቢሮ ቀርቦ መውሰድ ይችላል።
2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ የብር መጠን 1/4 (አንድ አራተኛ) በተረጋገጠ የባንክ የክፍያ ማዘዣ/ሲ.ፒ.ኦ/ በኤልሳቢ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
3. ሐራጁ የሚከናወነው አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጃክሮስ አካባቢ ወደጎሮ መታጠፊያ 100 ሜትር ገባ ብሎ ብርሃን ባንክ ያለበት ሕንፃ ጎን የሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ነዉ።
4. የንግድ ማህበራትን ወክሎ ለመጫረት የማህበራቱን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበራቱ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።
5. ተበዳሪው (መያዣ ሰጨው) በሃራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገርግን ባይገኙም ሃራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
6. ንብረቱን ለመጎበኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ፕሮግራም በማስያዝ በስራ ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በመገኘት መጎብኘት ይችላሉ።
7. የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለተቋሙ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
8. ለጨረታ የቀረበውን ተሸከርካሪ አሸንፎ የገዛ ተጫራች ከገዛው ተሽከርካሪ ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያዎች፣ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ከስም ዝውውር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች ይከፍላል።
9. ተሽከርካሪውን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ / ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን(ተሸከርካሪውን) ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ተቋሙ ኃላፊነት አይወስድም:: ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
10. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 666 75793/ 011 673 2829 ይደውሉ።
Tender details
- Deadline: 2026-11-10
- Bid closing time: 11:30
- Bid opening: 2026-11-10 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Elsabi Microfinance Institution S.C
- Bid bond: 25%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Reporter (Oct 25, 2026)
- Posted at: 2026-10-26T13:38:55.000Z
- Source: Qelal Tenders