House and Building Sale

ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ. የቦታ ስፋት 483 ካ.ሜ የሆነ ት ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

ለጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነት

አበዳሪው ቅርንጫፍ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት

የጨረታ መነሻ ዋጋ

የጨረታዉ ቀን እና ሰዓት

ጨረታው የወጣው

ከተማ፣ ክ/ከ/ ወረዳ/ቀበሌ

የባለቤትነት መረጋገጫ ቁጥር

የቦታ ስፋት በካ.ሜ

1.

አቶ ዳንኤል ጣሰው ደበላ

ወ/ሮ የሺ ጌታቸው

የመኖሪያ ቤት

አብዲ ኖኖ

ሸገር ከተማ፣ መልካ ኖኖ ክ/ከተማ ቤሮ ወረዳ (ሻቃ ሞል ፊት ለፊት)

Bur/Q/du/ 688/2014

483 ካ.ሜ

8,017,167.94

ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከ4፡00-5፡00 ሰዓት ኦሮሚያ ባንክ አብዲ ኖኖ ቅርንጫፍ ውስጥ

ለመጀመሪያ ጊዜ

1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ባንክ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።

2. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል:: ባለ ዕዳዎቹ ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል።

3. የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ስዓት 5 ደቅቃ በፊት ይጠናቀቃል። የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ እስኪለይ ደረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል። በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።

4. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል።

5. በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል።

6. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር እና ታክስ፣ የሊዝ ክፍያ፣ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ከሽያጩ ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ይከፍላል። ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።

7. ውዝፍ የሊዝ ክፍያን በተመለከተ ከእዳ ተመላሽ ብር ካለ ከተመላሽ ብር ላይ የሚከፈል ሲሆን ተመላሽ ብር ከሌለ ግን የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያን ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል።

8. ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ።

9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 1372 ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት ወይም በ 011 260 1242 ወይም በ 09 12 67 77 95 ኦሮሚያ ባንክ አብዲ ኖኖ ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

10. ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-11-26 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Oromia Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Oct 25, 2026)
  • Posted at: 2026-10-26T13:47:50.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders