Generators

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ የተለያዩ አቅም ያላቸው ዩፒኤሶች፣ የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች እና ጀነሬተሮች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር FA- 05/2026/27

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ የተለያዩ አቅም ያላቸው ዩፒኤሶች፣ የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች፣ ጀነሬተሮች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ መግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ይኖርባቸዋል: -

1. የዕቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ከጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም የግብር መለያ ካርድ ያላችሁ ተጫራቾች ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ኢጆ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ ላገለገሉ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 በማስገባት ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ቦሌ መንገድ ከአፍሪካ ኢንሹራንስ ፊትለፊት፣ ከባንኩ ህንጻ አጠገብ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ከባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ።

2. የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የከፈሉበትን ስሊፕ እና የጨረታ ሰነዱን በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት ሱሉልታ አዲስ የተሰራዉ ክ/ከተማ ከዋና መንገድ ወደ ቀኝ 100 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ፒልከን ተብሎ በሚታወቀው የባንኩ ግምጃ ቤት ውስጥ በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ፒልከን ለሚገኘው ንበረት ጥቅምት 18 ፣ 19፣ 20 እና 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ሲሆን ቦታ መጎብኘት ይችላሉ።

3. እንዲሁም የተቃጠለ የመኪና ዘይት ከነበርሜሉ ያለበትን ሁኔታ ለመጎብኘት ቄራ በረት ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ጎፋ በሚወስደው ዋናው መንገድ 100 ሜትር እንደተጓዙ በቀኝ በኩል የባንኩ ጋራጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በማንኛውም የሥራ ሰዓት እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ድረስ መጎብኘት ይችላሉ።

4. ገዢዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ቦሌ መንገድ ራንግ ህንጻ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ።

5. ባንኩ የሚከተለው የማወዳደሪያ ዘዴ በሰነዱ ሰንጠረዥ ላይ ንብረቶቹ እንደተዘረዘሩት ዓይነት በተናጠል መስመር በመስመር ሲሆን ባንኩ የተሻለ ሆኖ ካገኘም በጥቅል ወይም በጅምላ ያወዳድራል።

6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጠቅላላ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር 10% (አስር በመቶ)ዉን በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ በተጨማሪም የጨረታ መነሻ ዋጋ ለሌላቸው የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

8. ተጫራች የሚገዛበት የመግዣ ዋጋ በግልጽ በዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በተቀመጠው መሠረት ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% መካተቱን ወይም አለመካተቱን ለይቶ መጻፍ ይኖርበታል፤ ነገር ግን አሻሚ ቦታ ላይ ወይም ሁለቱም ቦታ ላይ ተመሳሳይ ዋጋ ከጻፈ እና ምንም ካልተገለጸ ባንኩ የቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተካቶ እንደቀረበ ታሳቢ ያደርጋል።

9. አሸናፊ መሆናቸው የተገለፀላቸው ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያውን በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው ማንሳት ይኖርባቸዋል፤ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፖኦ ውርስ ይደረጋል።

10. ጨረታው ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም በ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።

11. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ራንግ ህንፃ 7ኛ ፎቅ የባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ቢሮ

ስልክቁጥር፡- 011 557 6174 ፖ.ሳ.ቁ.16936/አዲስአበባ/

የኦሮሚያ ኀብረት ስራ ባንክ /አ.ማ/

ማህበረሰቡን ማጎልበት፣ ህይወትን መለወጥ!


Tender details

  • Deadline: 2026-11-03
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-11-03 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Cooperative Bank of Oromia S.C.
  • Buyer's registered address: Dembel City Center
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Reporter (Oct 25, 2026)
  • Posted at: 2026-10-26T14:14:04.000Z
  • Buyer website: https://coopbankoromia.com.et/
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders