Textile, Garments and Uniforms

የWindows of Hope 2026 ፕሮጀክት አጋር ድርጅቶች ህብረት (በሃንድ ኢን ሀንድ ሆሊስቲክ ቺልድረን ሰርቪስ መሪነት) በድጋሜ ያወጡት የልብስ እና የቆዳ ስፌት ማሽን ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

Description

 በድጋሚ የወጣ የልብስ እና የቆዳ ስፌት ማሽን ግዥ  ጨረታ ማስታወቂያ

የWindows of Hope 2026 ፕሮጀክት ያሰባሰባቸው አስር አጋር ድርጅቶች ለቆዳ እና የጨርቃጨርቅ ስፌት ማሽኖች አቅርቦት ብቁ የሆኑ አቅራቢዎችን በድጋሜ በጨረታ አወዳድረው መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በአጋር ድርጅቶቹ በሚመራው የቴሌግራም ቦት @WoH_ bid_ portalbot በኩል ወይም በጥምረቱ በተመረጡ ሁለት መስሪያ ቤቶች ማለትም በሃንድ ኢን ሀንድ ዋና መስሪያ ቤት (አድራሻ:- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፣ ከጀሞ ሚካኤል ወደ አየርጤና በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን 4ኛ ፎቅ) ወይም በዱካ ዩዝ ሌድ ኦርጋናይዜሽን (አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከቤተ መንግሥት ወደ ሴቶች አደባባይ በሚወስደው መንገድ ከጥይት ቤት ዝቅ ብሎ፣ ጃምቦ ፕላዛ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302) በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

ተወዳዳሪዎች ለጨረታ የሚያቀርቡትን ዋጋ ከጨረታው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ከሞሉ በኋላ፣ የጨረታ ማስከበሪያ በሃንድ ኢን ሀንድ ሆሊስቲክ ቺልድረን ሰርቪስ (Hind) ስም በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ወይም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሰነድ (Bid Security/Bond) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው በፓስታ በማሸግ ከጥቅምት 19 እስከ ህዳር 03 ቀን 2019 ዓ.ም 4:30 ድረስ በህብረቱ መሪ ድርጅት (ሃንድ ኢን ሀንድ) ዋና ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

ተጫራቾች በአንዱ የማሽን አይነት ወይም በሁለቱም መወዳደር የሚችሉ ሲሆን፣ ለእያንዳንዱ የማሽን አይነት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

የጨረታው ሣጥን ህዳር 03 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 ተዘግቶ 5:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ጨረታውን አሸንፈው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማያስረክቡ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት ዋስትና በሙሉ ለጥምረቱ አባላት ገቢ ይሆናል። ጨረታውን ለማያሸንፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል።

ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከሞሉ በኋላ በጥምረቱ መሪ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ሀንድ ኢን ሀንድ ሆሊስቲክ ቺልድረን ሰርቪስ (HinH) ቢሮ (አድራሻ፦ ጀሞ ሚካኤል፣ ወደ አየርጤና መንገድ 500 ሜትር እንደተጓዙ በሚገኘው ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን 4ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

ጥምረቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የጥምረቱ አባል ድርጅቶች፦

  1. ሀንድ ኢን ሀንድ ሆሊስቲክ ችልድረን ሰርቪስ (HinH) - በጥምረቱ መሪ ድርጅት
  2. ናሽናል ያንግ ውሜን ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን (NYWCO)
  3. አዲስ አበባ ሲቲ ዴቨሎፕመንት ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን (AACDCO)
  4. ሪዲም ዘ ጀነሬሽን (RTG)
  5. ፌይዝ ኢን አክሽን (FIA)
  6. ዱካ ዩዝ ሌድ ኦርጋናይዜሽን (DYLO)
  7. አይ ኬር ፎር ዘ ኔሽን (ICN)
  8. ቤተ ሳይዳ ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን (BCO)
  9.  ኢንዱራንስ ዩዝ አሶሴሽን (EYA)
  10. ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት (ECD)

ዱካ ወጣት መር ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-12
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-11-12 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Windows of Hope
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ የማሽን አይነት
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 26, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T07:40:06.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders