Stationery

የኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች (ቅጽ 1)፣ የፅዳት ዕቃዎች (ቅጽ 2) እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

 የጨረታ ማስታወቂያ

የኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሕጋዊ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ።

  • ቅጽ 1.የጽሕፈት መሣሪያዎች
  • ቅጽ 2 የፅዳት ዕቃዎች
  • ቅጽ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ለመጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢየሆኑ ፣ የሚቆርጡ እና ፐ ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 በመከፈል መግዛት ይችላሉ።
  5. በ15ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የድርጅቱ ባለቤት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
  6. ፍርድ ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard በታች ማቅረብ አይቻልም።
  7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም።
  8. ፍርድ ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደአስፈላጊነታቸው (25%) በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።
  9. ፍርድ ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት ለተከታታይ 6 ወራት ውል ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ይዋዋላል።
  10. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሠረት ተሟልተው ካልቀረቡና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው።
  11. የሚቀርቡትን ዕቃዎች አይነት ናሙና/ ዘውትር በሥራ ሰዓት መ/ቤታችን ድረስ ማምጣት ይችላሉ፡፡ ማንኛውም ናሙና ኦሪጅናል መሆን አለበት/ ።
  12. ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች አቅራቢው ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ገቢ ያደርጋል።
  13. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ብር 4000/አራት ሺ/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
  14. አሸናፊዎች በሚገቡት ውል መሰረት ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ለውል ማስከበሪያ የተያዘው የተመሰከረለት ሲፒኦ ውሉ መፈጸሙ እስኪረጋገጥ ድረስ ይቆያል።
  15. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ በፍጹም አይቻልም።
  16.  ፍ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት

ለተጨማሪ መረጃ፡- 0911082154 /0912348437

የኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-09
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 11:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-10 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Kura Jida Sub City Woreda Court
  • Bid bond: 4000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 26, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T07:51:21.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders