Equipment and Accessories

በሰሜን ወሎ አስተዳድር ዞን የቆቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ አካባቢ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የጽ/መሳሪያ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሰሜን ወሎ አስተዳድር ዞን የቆቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ አካባቢ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ

  1. የጽ/መሳሪያ እና 
  2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። 

በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና (ቲን) ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ቆቦ ከተማ አስ/ር ገን/አካ/ኢኮ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የተዘጋጀውን የእቃ እና የጨረታ መመሪያ የያዘ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላትና በፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ካስገቡ በኋላ በዚሁ ሰዓት ታሽጉ ከረፋዱ 4፡30 ላይ ይከፈታል።
  5. ጨረታው በየሎቶቹ በጥቅል ድምር በሎት ስለምትወዳደሩ የሁሉንም እቃዎች አገልግሎት ዋጋ መሙላት ግዴታ ነው።
  6. ጫረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ታሽጎ በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል።
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. መ/ቤቱ በግዥ ሂደቱ ላይ 20 በመቶ ከፍና ዝቅ ብሎ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 334 06 48 /00 68 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የቆቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-10
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-10 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Kobo City Administration FEDB
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published on: Be'kur (Oct 26, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T08:00:59.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders