Stationery
ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የመደበኛ ዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
በደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጨራቾች እንድትወዳደሩ እያሳወቅን።
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
የሎት አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን (በኢትዮጵያ ብር) |
|
1 |
ስቴሽነሪ እና ቶነሮች |
ሎት1 |
12,000 ብር |
|
2 |
የፅዳት እቃዎች |
ሎት2 |
11,000 ብር |
|
3 |
የደንብ ልብስ ፤የዴኬር እቃዎች እና የምርቃት ጋዎን |
ሎት3 |
30,000 ብር |
|
4 |
የቢሮ ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር እቃዎች |
ሎት4 |
50,000 ብር |
|
5 |
የመኪና አላቂና ቋሚ እቃዎች |
ሎት5 |
10,000 ብር |
|
6 |
የኤሌክትሪክና የቧንቧ ጥገና እቃዎች |
ሎት6 |
10,000 ብር |
|
7 |
የእንጨት ስራ ት/ክፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት7 |
40,000 ብር |
|
8 |
የጋርመንት እና ሌዘር አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት8 |
40,000 ብር |
|
9 |
የአውቶሞቲቭ ት/ክፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት9 |
40,000 ብር |
|
10 |
የከተማ ግብርና ት/ከፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት10 |
20,000 ብር |
|
11 |
የሆቴል ምግብ ዝግጅት፣ፀጉር ስራ ት/ክፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት11 |
15,000 ብር |
|
12 |
የአይሲቲ ት/ክፍል አላቂ እና የጥገናና የስልጠና እቃዎች |
ሎት12 |
10,000 ብር |
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- ከላይ በተጠቀሱት በየዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እስቴ ታክስ (የሻት ሠርተፍኬት) ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- በአቀራቢዎች መመዝገቢያ ላይ ራሳቸውን የመዘገቡ
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥር/10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት በደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መ/ግ/ቡድን የማይመለስ ለየአንዳንዱ ሎት 300 ብር(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ በሚወዳደሩበት ሎት የተጠየቀውን ሰነድ ዋናውን ይዘው መምጣት ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች ሲፒአ (CPO) ደጃዝማች ገረሱ ዲኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ስም ማሰራት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በእያንዳንዱ ላይ ሻትን ያጠቃለለ መሆን አለበት ዋጋው ሻትን ያላጠቃለለ ከሆነ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራቾች የሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ ፍሉድ የተጠቀመ ከሆነ እና በጉልህ የማይነበብ ከሆነ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች ተወዳድረው የሚያስገቡት ዕቃ ደረጃውን የጠበቀ መሆን እንዳለበትና በተወዳደረባቸው ሎቶች በሙሉ ከጨረታው ቀደም ብሎ የዕቃዎች ናሙና ማቀረብ ይኖርባቸዋል ናሙና ያልቀረበባቸው የዕቃ ዓይነቶች ከውድድር ውጪ ይሆናሎ።
- ተጫራቾች የወሰዱትን/የገዙትን የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ሰነድን ሙሉ በሙሉ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ ሰነዱን ሙሉ ለሙሉ ካልተመለሰ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች የመደበኛ ጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ሰነድ እና ፋያናሻል ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጥል በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ በማሸግ በአንድ ፖስታ በማጠቃለል አሽገው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል በተጨማሪም
- አሸናፊው ተጫራቾች ያሸነፈውን ጠቅላላ ዕቃዎች ትራንስፖርትና አውራጅ የጉልበት ሰራተኛ በመመደብ ለኮሌጁ ንብረት ድረስ በማምጣት ግቢ ማድረግ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ሲያሸንፍ 10 (%) ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሳጥኑ በ11ኛው ቀን በጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጅ መግቡድን ይከፈታል።
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በበዓላት ቀን እሁድና ቅዳሜ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
- ኮሌጁ 20% ያሸነፉበትን እቃ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማሳሰቢያ፡- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አድራሻ፡- ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መ/ግ/ቡድን ሲቁጥር 0112739712 ልዩ ስሙ - ከመሳለሚያ ሠፈረ ሠላም ወደ መድሃኒዓለም ት/ቤት በሚወስደው አስፋልት ያኔት ኮሌጅ ከፍ ብሎ
ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-11-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በጠዋቱ 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-11-06 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በጠዋቱ 4፡30 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Geresu Duki Industrial College
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Oct 26, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T08:02:09.000Z
- Source: Qelal Tenders