Equipment and Accessories

የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ኤሌክትሮኒከስ፣ ፈርኒቸር፣ ሞተር ሳይክሎች እና ጀኔረተር ተጫራቾችን በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት ለቴፒ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች

  •  ሎት1፡- ኤሌክትሮኒከስ
  • ሎት 2፡- ፈርኒቸር 
  • ሎት 3- ፡ ሞተር ሳይክሎች
  • ሎት 4- ፡ ጀኔረተር ተጫራቾችን በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁም መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች ለ2019 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው::
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ከፒ ማቅረብ አለባቸው::
  3. ተጫራቾች የቫት (የተጨማሪ እሴት ታክስ) ተመዝጋቢነት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የአቅራቢነት ሰርትፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው::
  5. ተጫራቾች ለ2018 በጀት አመት ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ኪሊራንስ ማቅረብ አላባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ጨረታውን ሲያቀርቡ ለጨረታ ማስከበርያ የሚሆን
    •  ለሎት/1/ 15,000 (አስራ አምስት ሺ ብር) 
    • ለሎት /2/ 10,000 (አስር ሺ ብር)
    • ለሎት /3/ 20,000 (ሀያ ሺ ብር)
    • ለሎት /4/ 20,000 (ሀያ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቴፒ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት በገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው::
  7.  ተጫራቾች ጨረታውን ሲያሸንፉ ለጨረታ ውል ማስከበርያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በእለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ቴ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 45 በመቅረብ ብር 500 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 21 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡በእለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን እቃ ማቴርያል/ ቴ/ከ/አስ/ር ግ/ን/አር ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ሸካ ዞን

የቴፒ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-17
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 21 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-11-17 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 21 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: South West Ethiopia Region Sheka Zone Masha Woreda F/E/D/Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T08:31:33.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders