House and Building Sale

የቤቶች ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ አይናለም አበበ እና የፍ/ባለዕዳ ብዙነሽ ዘለቀ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በ25/07/2018ዓ.ም በተደረገው በእርቅ ስምምነት መሰረት እና በኮ/መ/ቁ/217568 በ30/10/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት

1ኛ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 46 በአቶ ዘለቀ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ሰነድ አልባ ቤት ያረፈበት 30 ካ/ሜ ከግቢው በፕሮፖርሽን 63ካ/ሜ የሚደረሰው ሲሆን በ1988 አየር ካርታ (GIS ላይ የሚታይ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,437,424 ( ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ሃያ አራት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 21 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

2ኛ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 462 በእነ አማረች ተገኝ እጅጉ (7ሰዎች) ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የይዞታ መለያ ቁጥር AA000080304287/ 1የተመዘገበ የቤቱ ስፋት 45.08ካ/ሜ እና የይዞታ ስፋት ጠቅላላ በፕሮፖርሽን 154,39 ካ/ሜ ሁለቱም ቤቶች በአንድ ይዞታ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በይዞታ ውስጥ የቀበሌ ቤት ያለበት ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 4,804,462.4 (አራት ሚሊዮን ስምንት መቶ አራት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ሁለት ከ41/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 21 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ c.PO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡ ፡ የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25111 273-0852
በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-30
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-11-30 12:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T08:46:28.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders