Stationery

የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርስቲ ለ2019 በጀት ዓመት ለቢሮና ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ሸቀጣሸቀጥ እና የጽህፈት መሳሪያ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርስቲ ለ2019 በጀት ዓመት ለቢሮና ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ሸቀጣሸቀጥ እና ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

3. ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በየሎቱ በመክፈል በዩኒቨርሲቲው ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡

7. የሚገዙ የዕቃዎችን (አገልግሎቶች) ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከጥቅምት 16/2019 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በዩኒቨርሲቲው የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የተገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡

10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በዩኒቨርሲቲው ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጥቅምት 16/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

11. የጨረታ ሳጥኑ ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው አዳራሽ ይከፈታል፡፡

12. የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

13. ዩኒቨርስቲው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፡፡

15. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 23 60 በመደወል  ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-04
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-04 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Regional State University
  • Bid document price: 500.00 ብር በየሎቱ
  • Published on: Be'kur (Oct 26, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T09:08:37.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders