Stationery
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ 2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን የሥራ መገልገያዎች በአንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ 2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን የሥራ መገልገያዎች ሎት አንድ የፅህፈት መሳሪያዎች ሎት ሁለት ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ ሎት ሶስት የጽዳት እቃዎች፣ ሎት አራት የህትመት ሥራዎች፣ ሎት አምስት የደንብ ልብስ የአደጋና የጤና መጠበቂያ እቃዎች ፣ ሎት ስድስት የመኪና ዲኮር እቃዎች ፣ሎት ሰባት ቋሚ የአይቲና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት ስምንት የፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ መለዋወጫ እቃዎች በአንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው መወዳደር ይችላል።
1. የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢ ዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ።
2 ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ።
3. ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት።
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥራችን 1000383805035 በማስገባት እስሊፑን ይዘው የጨረታውን ሰነድ በሥራ ሰዓት ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሲኤምሲ ሚካኤል ፊት ለፊት ድልድዩ አጠገብ ዴሉክስ ፈርኒቸር ጀርባ ያው ህንፃ 4ተኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሠረት ዋናውንና ኮፒውን የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አሰር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ሙሉ ቀን ጨምሮ በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 2% በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል ስም በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው የሚከፈተዉ የጨረታ ማስታወቂያው 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ሙሉ ቀንን ጨምሮ አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ 11ኛው ቀን ከሰዓት 8:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 8፡30 ይከፈታል ። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል ። በተጨማሪም የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀንና ሰዓት በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል።
8. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ 0116 734 316 / 0116 732 106 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
አድራሻ፡- ሲኤምሲ ሚካኤል ፊት ለፊት ድልድዩ አጠገብ ዴሉክስ ፈርኒቸር ጀርባ ያለዉ ህንፃ 4ተኛ ፎቅ የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-07
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ሙሉ ቀንን ጨምሮ አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ 11ኛው ቀን ከሰዓት 8:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-07 14:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ሙሉ ቀንን ጨምሮ አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ 11ኛው ቀን ከሰዓት 8:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Lemi Kura Sub City Small Tax Payers Branch Office
- Buyer's registered address: ሲኤምሲ ሚካኤል ፊትለፊት ዲሉክስ ፈርኒቸር ጀርባ ያለው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T10:58:26.000Z
- Source: Qelal Tenders