Hand Tools and Workshop Equipment

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለይዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

እነርሱም፡-

1. የቧንቧ መፍቻ (Pipe wrench) እና ጥርስ ማውጫ ዕቃዎች

2. የውሃ መስመር ዝርጋታ ዕቃዎች (የተለያዩ ፊትንጎች)

3. የጽሕፈት መሣሪያዎች (Stationary)

4. ሞተር ሳይክል

5. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

6. የፅዳት ዕቃዎች

7. የቢሮ ዕቃዎች

8. የመኪና ጎማ እና የተለያዩ ዘይቶች

በ2019 ዓ.ም 1 ዙር ግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች የወጡ መስፈርትና ተጫራቾቹ ሊያከብሩትና ሊጠብቁት የሚገባ ነጥቦች ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ በመከተል ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

1. በጨረታው ለመካፈል ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (Taxs) ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ እስፔስፊኬሽን ሙሉ በሙሉ መረዳት ይኖርባቸዋል።

5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።

6. ድርጅቱ የሚጫረታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።

7.የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት ተሟልተው ካልቀረቡና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው፡፡

8. ማንኛውም ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዓይነት ነጠላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በቁጥር በተጻፈው ዋጋና በፊደል በተጻፈው ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር በፊደል የተጻፈው ይወሰዳል፡፡

9. ጨረታውን ያሸነፈው አቅራቢ (አቅራቢው ድርጅት) በራሱ ትራንስፖርት የመ/ቤቱ ግምጃ ቤት (መጋዘን) ድረስ በማምጣት ዕቃዎቹን ገቢ ያደርጋል።

10. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን ዕቃዎች ጭነው ለማቅረብ ድርጅቱ ጋር ውል ይፈራረማሉ፡፡ ውሉ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ሊራዘምም ላይራዘምም ይችላል።

11. ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው ጽሕፈት ቤት የዋስትና ደብዳቤ ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡

12. በጨረታ የተሸነፉትም ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ በዋስትና ያስገቡት ገንዘብ ወይም CPO ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

13. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡

14. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ላይ የዕቃዎቹን መስፈርቶች አይነት መጠንና ብዛት በትክክል ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።

15. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት፡፡

16. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የድምር ስህተት ካስቀመጡ ድርጅቱ የማይቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

17. ማንኛውም ተጫራች የሚያስገባው ሰነድ በጥንቃቄ ታሽጎ ፋይናንሻል (financial) አንድ ኦሪጂናል ሁለት ኮፒ እና ቴክኒካል (technical) የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ጊንቢቹ ፈንታሌ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም፡፡

18. በቢሮ ወንበርና ጠረጴዛ ፣ የውሃ ቆጣሪ (water meter) ፣ 3/4 ቧንቧ ውሃ ዝርጋታ ዕቃዎች ላይ የምትወዳደሩ ተጫርቾች ናሙና ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

19. የጨረታውን ሰነድ ከጥቅምት 17/02/2019 እስከ 08/3/2019 ዓ.ም ድረስ ሰነዱ ይሸጣል፡፡ በዚያው ዕለት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን 5፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾቹ ካልተገኙ ድርጅቱ የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ዕለቱ በአል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡

20. የሚቀርቡት ዕቃዎች 1ኛ ደረጃ መሆን ይኖርባቸዋል፤ ለማሸነፍ ብሎ ዕቃውን የማይመጥን ያልሆነ ዋጋ ሞልቶ ወይም ሰጥቶ ዕቃው ሲቀርብ 2ኛ ደረጃ ከሆነ የማንቀበል መሆኑን አስቀድመን እንገልፃለን፡፡

21. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ) እያንዳንዱ ዝርዝር ላይ በመክፈል በሞጆ ከተማ በሚገኘው የጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በግዢ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7 ክፍል ቀርበው ማግኘት (መግዛት) የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

22. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሠረት ጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያ እና በስልክ እንደተገለጸ በ7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ሞጆ ከተማ በሚገኘው ጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ጋር መፈራረም አለበት፡፡

ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታቸውን ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።

23. መሥሪያ ቤቱ ከሚያደርገው የግዥ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን መገንዘብ አለባቸው፡፡

24. አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለጸለት ዕቃ ብዛት አባዝቶ የጠቅላላውን ዋጋ 10% የውል ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ለጊንቢቹ ፈንታሌ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

25. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

26. በፖስታውና በሰነዱ ላይ ሕጋዊ ማህተም ፣ ስልክ ቁጥር እና ፊርማ መኖር አለበት፡፡

ለበለጠ መረጃ ሞጆ ከተማ በሚገኘው የጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስልክ ቁጥር፡-022-236-74-77 ነው

ማሳሰቢያ፡-

  • ማንኛውም ተጫራች ድርጅት የሚወዳደርበትን ሙሉ ስፔስፊኬሽን በጥሞና አረጋግጦ መረዳት ይኖርበታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ስህተት ምንም አይነት ማስተካከያ የማናካሂድ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
  • የተጫራቾች መገምገሚያ መስፈርት በተመለከተ በቴክኒክ መመዘኛ በትክክል በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን እና በሰነድ ላይ የተጠየቁትን ሕጋዊ የሆነ ነገሮችን አሟልቶ በፋይናንስ ውድድር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው የጨረታው አሸናፊ ይሆናል።
  • ከዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ በታች 0.5 % የተገለጸው የውሃ ፈንድ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባወጣው የአዋጅ ቁጥር 233/2013 እና በደንብ ቁጥር 236/2015 በወጣው የአፈጻጸም ደምብ መሰረት መሆኑን አውቃችሁ ተገቢውን ክፍያ እንድትከፍሉ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
  • አቅራቢዎች የጨረታ ማስታወቂያው ላይ በቁጥር በቀረበው መሰረት በቅደም ተከተላቸው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ማንኛውም ተጫራች ለመ/ቤቱ ባላቸው ዕቃዎች ላይ የዕቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • አሸናፊው ያሸነፈበትን የዕቃ አይነት አሸናፊ መሆኑን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ የዕቃውን ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡

አድራሻ፡- ሞጆ ፋና ትምህርት ቤት አጠገብ ወይም ወደ ፈጣን መንገድ መውጫ።

ለበለጠ መረጃ:- ጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

ስልክ ቁጥር - 022-236-74-77.

በምስራቅ ሸዋ ዞን የጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-17
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-17 11:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ginbichu Fentale Drinking Water and Sewage Service Organization
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 1,500.00 ብር እያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T11:18:24.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders