House and Building Sale
ከአጠቃላይ ይዞታው ላይ በፕሮፖርሽን 145.74 ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ፍሬህይወት የማነብርሃን እና በፍ/ባለእዳ እነ አቶ አዲሱ የማነብርሃን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.212062 በየካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/217746 23/10/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 1580 የካርታ ቁጥር 11/80/5875/00 የሆነ ከአጠቃላይ ይዞታው ላይ በፕሮፖርሽን 145.74 ካ/ሜ አዋሳኞቹ በስተሰሜን ርስቱ ፋንታዬ በስተደቡብ መንገድ በስተምዕራብ መንገድ በስተምስራቅ የቀበሌ ቤት ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 6,715,949.58 (ስድስት ሚሊዮን ሰባት መቶ አስራ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ዘጠኝ ብር ከ58/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሠርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-27
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-11-27 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T11:25:28.000Z
- Source: Qelal Tenders