Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሱሉልታ ዋና ቅርንጫፍ በ2019 የበጀት ዓመት የጽዳት ዕቃዎችን፣ የቧንቧ ዕቃዎችን፣ የደንብ ልብሶችን፣ እስቴሽነሪ (የፅህፈት ዕቃዎችን) እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሱሉልታ ዋና ቅርንጫፍ በ 2019 የበጀት ዓመት፤  የጽዳት እቃዎች፣ የቧንቧ ዕቃ፣ የደንብ ልብሶች፣ እስቴሽነሪ /የፅህፈት ዕቃዎች እና ኤሌትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለፀውን መመሪያ በመከተልና ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲሳተፉ ታጋብዘዋል።

የጨረታ መመሪያ፡-

1. ተጫራቾች በ ጨረታ ለመካፈል በዘረፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ አሴት ታክስ /ሞማ/ ማሽቃ ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢች ዝርዝር የተመዘገቡና ግብር መከፈሉን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰንድ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ሰነዱን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 500 /አምስት መቶ/ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለያንዳንዱ ሎት በብር 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ እና ባንክ ገራንት /An unconditional Bank Guarantee ማስያዝ አለበት።

5. ጨረታው በ15ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰአት ላይ ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ባለቤቱ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል። በለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።

6. ተጫራቾች ሙሉ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ፣የድርጅ ታቸውን ማህተም በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መፃፍ አለባቸው።

7.ተጫራቾች 3% ዊዝሆልዲንግ መክፈል አለባቸው።

8. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ የተፃፈ መሆን አለበት።

9. ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ጨረታው ላይ ሲቀርብ /ለመሳተፍ ሙሉ የኦዲት ሪፖርት የ2018 ዓ.ም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

10. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ የመቆያ ጊዜ (Price Validity date) ከጨረታው መክፈቻ እለት ጀምሮ የሚጸናበትን ጊዜና ስራውን አጠናቆ የሚያስረክብበት ጊዜ 120 /አንድ መቶ ሀያ ቀናት (Delivery time) ውስጥ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

11. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. የሚገዙ ዕቃዎች በተሠጠው እስፔስፊኬሽን መሠረት ተሟልቶ ካላቀረቡ ና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈፀም ኃላፊነቱን የ አቅራቢው ድርጅት ነው።

3. ድርጅቱ የሚያጫርታቸውን እቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው (25%) በመጨመር ወይም በመቀነስ ይችላል።

14. የዕቃዎቹ ዋጋ የሚከፈለው ዕቃዎቹ በግምጃ ቤታችን ገቢ ከሆኑ በኃላ ነው።

15. የሚቀርበው ዋጋ በሙሉ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።

16. ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች አቅራቢው ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል።

17. ከዚህ በላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ሳይወጡ ወይም ውሉን በ አግባቡ ሳይፈፅም ቢቀር ለውል ማስከበሪያ ዋሰትና የተያዘው ገንዘብ ለጽ/ቤቱ ገቢ ይሆንና አስፈላጊ የህግ ቅጣቱንም የሚቀበል ይሆናል።

18. ተጫራቹ የጽዳት እቃዎችን፣ ለደንብ ልብሶች እና የቧንቧ ዕቃዎች ላይ ለ እያንዳንዱ እቃ የእቃ ዓይነት ላይ በተጠየቀው መሠረት ናሙና ማቅረብ አለበት።

19. ለኤሌትሮኒክስ እቃዎች ላይ የዕቃው ካታሎግ መቅረብ አለበት።

20. ተጫራቹ ካሁን በፊት በጨረታ ከተሳተፈባቸው የመንግስትና የግል ድርጅቶች የዕውቅና ሠርተፊኬት ማቅረብ አለበት።

21. በጨረታው ለግዢ የቀረቡ እቃዎች በሙሉ ጋራንትድ መሆን አለባቸው።

22.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው 50000 /ሀምሳሺ/ ብር እና ባንክ ገራንት/nonconditional Bank Guarantee አሸናፊው አካል ዕቃውን አስገብቶ እስኪጨርስ ድረስ የማይመለስ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።

23. ያሸነፈው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10% ለውል ማስከበሪያ ያሲዛል፤ እቃውን ሙሉ በሙሉ የማያቀርብ ከሆነ የውል ማስከበሪያው የማይመለስ ይሆናል።

24. ተጫራቹ በቧንቧ ዕቃዎች ላይ ካሸነፈ የውሃ ፈንድWetr Fund/ 0.5% የሚከፍል ይሆናል::

 በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሱሉልታ ቅርንጫፍ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-10
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ15ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-11-10 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በ15ኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰአት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Sheger City Water Supply and Sewerage Service Enterprise 
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T11:29:26.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders