Equipment and Accessories
በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኘው ለጃናሞራ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም የበጀት ዓመት የተለያዩ ግዥዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsSolar and Photovoltaic
Amhara
More tags
Energy, Power and ElectricityMachinery and EquipmentAgriculture and FarmingStationeryOffice Supplies and ServicesTest & Measurement ToolsHand Tools and Workshop EquipmentPoultry, Bee and Animal HusbandryWood and Wood WorkingMetal and Metal WorkingAmharic2merkatoJanamora Woreda Finance and Economic Development Bureau
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኘው ለጃናሞራ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም የበጀት ዓመት በሴጎርፕ ፕሮጀክት የበጀት ድጋፍ
- ሎት 1. የሶላር መብራት፣
- ሎት 2. የልማት መሳሪያዎች ማለትም ዶማ፣ ቀጭኑ ሲባጎ ገመድ፣ ውሃ ልክ፣
- ሎት 3. እስቴሸነሪ /የጽህፈት መሳሪያዎች/ እንዲሁም
- ሎት 4. ዘመናዊ የንብ ቀፎ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ (ቲን) ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የግብር ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ ሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በእያንዳንዱ ሎት የዕቃዎቹን አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ)፣ (ቢድ ቦንድ) ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከጥቅምት 16/2019 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 25/2019 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከጥቅምት 16/2019 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 25/2019 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 ጥቅምት 26/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡15 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ (በሎት) ድምር ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ወድቅ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ስምና ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡
- ተጫራቾች የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመዉ ጃ/ወ/መ/ብርሃን ግብርና ንብረት ክፍል ሲሆን ተጫራቾች ትራንስፖርት አንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-05
- Bid closing time: 10:15
- Bid opening: 2026-11-05 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Janamora Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: 2% ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Be'kur (Oct 26, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T11:48:30.000Z
- Source: Qelal Tenders