Food and Beverage
በምሥራቅ ጎጃም ዞን የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግብርና ጽ/ቤት የሚገኘዉን ለምግብ አገልግሎት የሚዉል ስንዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምሥራቅ ጎጃም ዞን የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግብርና ጽ/ቤት የሚገኘዉን ለምግብ አገልግሎት የሚዉል ስንዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በጨረታ ቁጥር ጎ/0002/2019 ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለዉ ወይም በኢትዮጵያ ህግ መሰረት የተቋቋመ የንግድ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት በሚገኘው ፋይናንስ ቡድን ረዳት ገንዘብ ያዥ የስራ ክፍል ድረስ በመምጣት የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በጎ/ሲ/እ/ወ/ገንዘብ /ጽ/ቤት የኢትጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000106590463 የአባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 4052118179901017 ላይ ገቢ በማድረግና ያስገቡበትን የባንክ ስሊፕ ይዘው በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ስንዴዉን ጎ/ሲ/እ/ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 23,000 (ሃያ ሶስት ሽህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለጨረታ ማስገቢያ በሚል ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
- የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ከግንደወይን ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አባይ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ የመዝጊያ ጊዜ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጎ/ሲ/እ/ ወ/ገንዘብ /ጽ/ቤት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ5 (አምስት) የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ስንዴ በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ የሚዛንና ሌሎች ወጪዎችን በመሸፈን ስንዴዉ ከሚገኝበት ስፍራ ቅርብ በሆነ ሚዛን በማስመዘን ውል ከፈረሙ በኋላ በ10 /አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ ስንዴዉን በማንሳት ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡ ግምታዊ መጠኑ የስንዴ መጠን ጋር የሚኖረው ልዩነት ታስቦ አሸናፊው ተጫራች ተጨማሪ ክፍያ የሚኖርበት ከሆነ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ልዩነት የሚኖረውን ሂሳብ መክፈል ያለበት ሲሆን በትርፍነት የሰጠው ተመላሽ የሚደረግለት ገንዘብ ካለም በአገልግሎቱ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች እራሳቸዉን ከወድድሩ ቢያገሉ የጨረታ ማስከበሪያዉ ለመንግስት ገቢ የሚደረግ መሆኑን እገልጻለን፡፡
- ጽ/ቤቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ወይም ሌላ ጨረታውን ለመሰረዝ የሚያበቃ ምክንያት ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 664 04 64 /002 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-11
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30
- Bid opening: 2026-11-11 10:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Goncha Siso Enese Woreda FEDB
- Bid bond: 23,000 (ሃያ ሶስት ሽህ ብር)
- Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Be'kur (Oct 26, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T13:08:53.000Z
- Source: Qelal Tenders