Printing and Publishing
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2019 በጀት አመት ዓመታዊ የህትመት ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2019 በጀት አመት ዓመታዊ የህትመት ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፤ ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ እና ንብረት አስተዳዳር ቡድን በቢሮው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 10 ቀን በጋዜጣ ታትሞ የሚውል ሲሆን፤ በ16ኛው ቀን ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 02 56 65 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት
ባሕር ዳር
Tender details
- Deadline: 2026-11-05
- Bid closing time: 09:00
- Bid opening: 2026-11-05 09:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara National Regional State Supreme Court
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Be'kur (Oct 26, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T13:12:16.000Z
- Source: Qelal Tenders