House and Building Sale
የቤቱ ስፋት 664 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመበት እነ የሟች አቶ አንድዬ ተሰማ ሀይሉ ሚስት እና ወራሾች እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ገብረእየሱስ ደስታ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 310432 በ18/06/ 2016ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ 319967 በ02/11/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በለጠው ትዕዛዝ መሠረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የካርታ ቁጥር የካ/205902/11 የሴሪያል ቁጥር 0123659 የሆነ ይዞታ በልማት ምክንያት በመፍረሱ የተሰጠው ምትክ ቦታ ሲሆን በአቶ ገብረእየሱስ ደስታ ስም የተመዘገበ የቤቱ አገልግሎት ለንግድ የሆነ የይዞታ ስፋት 197 ካ.ሜ አጠቃላይ የተገነባው ግንባታ የቤቱ ስፋት 664 ካ.ሜ የሆነ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 23,413,940.68 (ሃያ ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ አስራ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ከ68/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የፍ/አፈ ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852
በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-27
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-27 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Oct 28, 2026)
- Posted at: 2026-10-28T08:18:15.000Z
- Source: Qelal Tenders