Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የደሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ እና በስሩ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች እንዲሁም የመኪና መለዋወጫ እቃዎች የጎሚስታ ጥገና አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የደሴ ከተማ አስ/ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ እና በስሩ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች እንዲሁም የመኪና መለዋወጫ እቃዎች የጎሚስታ ጥገና አገልግሎት ለማገኘት፡-

  • ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያ
  • ሎት 2 የፅዳት እቃዎች
  • ሎት 3 ቋሚ እቃዎች
  • ሎት 4 የህንፃ መሳሪያ
  • ሎት 5 የከባድ እና የቀላል ተሽከርካሪዎች ጎሚስታ
  • ሎት 6 የቀላል ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ
  • ሎት 7 የከባድ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ
  • ሎት 8.ቢሸፍቱ የከተማ አውቶብስ መለዋወጫ
  • ሎት 9.የከባድ ተሽከርካሪዎች የጋራጅ ጥገና አገልግሎት
  • ሎት 10 የቀላል ተሽከርካሪዎች የጋራጅ ጥገና አገልግሎት
  • ሎት 11 የከባድ እና የቀላል ተሽከርካሪዎች ጎማና ባትሪ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር አሸናፊ በመለየት አመታዊ ውል ይዞ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ ከዚህ ባታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።

1. በዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ

2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላችሁ እና የብቃት ማረጋገጫ ወረቀት ማቅረብ የሚችል

3. ግዥው ከ500000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ከፋይነት ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ከላይ ከ እስከ 3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎችን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር 300 ብር ከግዥ ፋይናንስ አዲሱ ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 18 ላይ በመምጣት ከ18/2/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 27/2/2019 11፡30 ድረስ ደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በግዥ ፋይናስ ቡድን አዲሱ ቢሮ 3ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

6. የሚገዙ እና የሚሰሩት አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታው ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ። የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝና ፍሉድ መደረግ የለበትም።

7. ተጫረቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ድምር 2% ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / ሲፒኦ ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው እንዲሁም አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፉበትን ዋጋ 10% የውለታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ደሴ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በግዥና ፋይናንስ ቡድን አዲሱ ቢሮ 3ኛ ፎቅ ላይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በ30/2/2019 ዓ.ም 3፡30 ድረስ ሰነዱን በማስገባት ይታሸጋል።

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 30/2/2019 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ ደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በግዥ አዲሱ ቢሮ 3ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል።

10. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል።

11. ውድድሩ የሚካሄደው በጥቅል ድምር ወይም በሎት ድምር ውጤት ነው።

12.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስ.ቁ 033 312 0617 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

የደሴ ከተማ አስ/ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-09
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-11-09 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Dessie City Adminstration Urban Infrastructure Development Command
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 28, 2026)
  • Posted at: 2026-10-28T08:59:45.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders