House and Building Foreclosure
አማራ ባንክ አ.ማ መኖሪያ ቤት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር አማራ ባንክ 56/2019
አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪው ቅርንጫፍ
|
የንብረቱ አድራሻ |
የቦታው ስፋት
|
የባለቤትነት ማረጋገጫ ሠነድ ቁጥር |
የንብረቱ ዓይነት/የይዞታው አገልግሎት |
የጨረታ መነሻ /ብር/ |
ጨረታው የሚከናወንበት |
|||||
|
ክ/ከተማ |
ከተማ
|
ወረዳ |
ቀበሌ |
ቀን |
ሰዓት |
ቦታ |
||||||||
|
1 |
አስናቀ እጅጉ አንተነህ |
ወ/ሪት ቤዛዊት እጅጉ አንተነህ |
ሳር ቤት
|
ኮ/ቀራንዮ |
አዲስ አበባ
|
4 |
_ |
150 ካ.ሜ
|
K05/02-3-130-183-8260/01 |
ለመኖሪያ
|
8,128,007.98 |
ኅዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም |
ከ 4፡00 አስከ 5፡00 ሰዓት |
አማራ ባንክ አ.ማ ዋናው መስርያ ቤት |
ማሳሰቢያ
1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) ብቻ በአማራ ባንክ ኢማ ስም በማሰራት; በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
2. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው።
3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል። ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም፤ ለባንኩ ገቢ ይሆና። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሃራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል። ላላሽነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል።
4. የሐራጁ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ክፍያን ጨምሮ፣ ግብር፣ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዘዋወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው አሸናፊው/ ይከፍላል።
5. ተጫራቾች በሃራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፤ የመንጃ ፍቃድ፣ ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል:: ተጫራቾች የህግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሃራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
7. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርካዉትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል።
8. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ስዓትና ቦታ ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል። ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዣ ሰጪዉ ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል።
9. ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለስብ ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሊሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም። ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
10. በባንኩ የብድር ፖሊሲ፤ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ለተጫራቹ እስከ 100% ብድር ሊያመቻች ይችላል።
11. የተጫራቾች ምዝገባ ከሃራጁ መዝጊያ ሰአት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል።
12. በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅትም ያገለግላል።
13. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አማ 0115 58 27 64 ወይም 011 5 58 41 89 በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አማራ ባንክ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-11-27
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-11-27 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Amhara Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Oct 28, 2026), Addis Zemen (Oct 28, 2026)
- Posted at: 2026-10-28T11:42:29.000Z
- Source: Qelal Tenders