Printing and Publishing

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ብሮሸሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁ. ፋሀአዲ/ግዳ/003/2019

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከታች የተገለፁትን ብሮሸሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የህትመቱ ዓይነት

ብዛት

Amharic & English

Amharic & Afan Oromo

Amharic & Aaf Somali

1

Takaful

10,000

7,000

3,000

2

Life Insurance

13,000

7,000

……

3

General Insurance

13,000

7,000

……

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

1- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረገጹ (Website) አትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

2- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ ፣የግብር መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።

3- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 18 ቀን 2019ዓ.ም ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ደረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

4- ተጫራቾች ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (cpo) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5- ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ህዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም ህዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም. በግዥ ዳይሬክቶሬት የስብሰባ አዳራሽ በ8፡30 ይከፈታል።

6- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-551 2400 የውስጥ መስመር 217/262 ወይም በቀጥታ 011-550 4931 መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-17
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-11-17 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Insurance Corporation
  • Bid bond: 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 29, 2026)
  • Posted at: 2026-10-29T07:30:15.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders