House and Building Sale
በድጋሚ የወጣ የይዞታው ስፋት 208 ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ዝናቤ ሲሳይ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ነጋሽ ሄይ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.184668 በ03/10/2016ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/ መ/ቁ.209946 በቀን 30/7/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር9999/1አዲስ/ በቁጥር YK117184459208272 የተመዘገበ ካርታ ያለው የይዞታ ስፋት 208ካ/ሜ በልኬት የተገኘው የቦታ ስፋት 236 ካ/ሜ ሲሆን ይህን በልኬት የተገኘ ስፋት በስተምስራቅ በኩል በከፊል ከአጎራባች ጋር ያለው ድንበር በወሰናቸው መሰረት የታጠረ ባለመሆኑ በልኬት የተገኘው የቦታ ስፋት ሊቀነስ ወይም ሊጨመር የሚችል ሆኖ ከአጠቃላይ ይዞታ በካርታ ከተያዘው ላይ 6ኛ ዙር የመንገድ ጥናት 9.56 ካ/ሜ ይነካዋል በካርታ መሰረት በሐራጅ የሚሸጠው በብሎኬት የተሰራ 3 ክፍል ሰርቪስ ቤቶች ወይም የ6ኛ ተስማሚ የአቶ ተመስገን ፋንታሁን ሲሳይ ቤት የተባለውን ሳይጨምር የ6ኛ ተስማሚ አቶ ተመስገን ፋንታሁን 3ክፍል ብሎኬት የተሰራውን ቤት ሳይጨምር እና 3ክፍል በብሎኬት የተሰራው የግል ቤት ስፋቱ 34.60ካ/ሜ ከቦታው ለቤቱ (3ክፍል ብሎኬት ቤቱ) በንጽጽር የሚደርሰው የይዞታው ስፋት 25.97ካ/ሜ የሆነ የሐራጅ መነሻ 5,902,340 (አምስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ አርባ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡
ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.209946 በቀን 10/02/2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 1,475,585 ( አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሰባ አምስት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ አምስት ብር) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 22 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትጵዮያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡፡ ከ/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤጽ/ስም C.P.O. አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ5 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-12-01
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-12-01 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Oct 29, 2026)
- Posted at: 2026-10-29T08:59:22.000Z
- Source: Qelal Tenders