Stationery

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የጉልበት ሥራ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና የተለያዩ ህትመቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 006/002/2019

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት ለማሟያ የሚሆን በአንደኛ ዘር ያልተከናወኑ የሁለተኛ ዘር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደረጃቸውን የጠበቁ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች የደንብ ልብሶች ቋሚ ዕቃዎች የጉልበት ስራ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናና ለአንድ አመት ኮንትራት የሚቆይ የተለያዩ ህትመቶች ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ በገ/ኢ/ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር (supplier List) ውስጥ የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀትና ማንኛውም ተወዳዳሪ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸው መረጃ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርጎ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል። በጨረታ መዝጊያ ሰዓት የሚመጡ ተጫራቾ ተቀባይነት አይኖራቸውም።

4. ተጫራቾች በጨረታው ማስታወቂያ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃ ዓይነቶች በሙሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሊሆን ይገባል።

6. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውን እንዲሁም ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም በማህተም ማረጋገጥ ይኖርባል።

7. ተጫራቾች በጨረታ የሚወዳደሩትን የዕቃ ዓይነቶች ለይተው መፃፍ አለባቸው።

8. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠ ድርጅት ዕቃዎችን ከወረዳው አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ጋር ውል በገባ 10 ቀናት ውስጥ ዕቃ ግምጃቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት አገልግሎት ወይም ወጪ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ የተጫረቱትን ዕቃ ዋጋ ጠቅላላ ድምር በሎት 2% በካሽ ማሳያ ማዘዣ እና ኮፒ በተደረገበት የጨረታ ሰነድ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. በጨረታው ያሸነፈው አካል ማሸነፉ እንደተገለጸለት ከመ/ቤቱ ጋር በ10 (አስር) ቀን ቀርቦ ውል መፈጸም አለበት።

11. በጨረታው ያሸነፈ አቅራቢ ውል ከጽ/ቤቱ ጋር ውል ካልፈጸመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ ተመላሽ አይሆንም።

12. በጨረታው ያሸነፈ አቅራቢ ውል ሲፈጽም የግዥውን አጠቃላይ ዋጋ 2% ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።

13 ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

14. የጨረታ ሳጥን በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 ይከፈታል። 11ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።

15. በጨረታው ላይ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ ለ60 (ስልሳ ) ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።

16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

  • ለበለጠ መረጃ : በስልክ ቁጥር 09 67 67 00 05/ 09 11 46 00 14/ 09 13 14 79 51/ 09 30 64 97 17
  • በመደወል ከድሪም ላይነር ሆቴል ወረድ ብሎ ወይም ከናዝራ ሆቴል ፊት ለፊት የድሮ 35 ቀበሌ ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል።

በቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ ዐ2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-09
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡30
  • Bid opening: 2026-11-10 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kirkos Sub City Woreda 02 Administration Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: በሎት 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 29, 2026)
  • Posted at: 2026-10-29T09:32:21.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders