Stationery

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ የዕቃ እና የአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019

የን/ስ/ላ/ክ/ከ/ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ የዕቃ እና የአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያ ፣
  • ሎት 2 የፅዳት እቃዎች መሳሪያ ፣
  • ሎት 3 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
  • ሎት 4 የኮምፒዩተር ፕሪንርና ፎቶ ኮፒ ጥገና፣
  • ሎት 5 የትራንስፖርት አገልግሎት ፣
  • ሎት 6 የተሸከርካሪ ጌጣጌጥና የመኪና ጎማ

በዚሁ መሰረት በዘርፉ የተሰማራችሁ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በሟሟላት መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
  2. የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  3. የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፤
  4. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ  መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. በጥቃቅን እና አነስተኛ ከአደራጅ መስሪያ ቤት የጨረታ እና የውል ማስከበሪያ የድጋፍ ደብዳቤ ቀጥታ ለአጫራች እቃ ግዥ መስሪያ ቤት የተፃፈ ማቅረብ አለበት፡፡
  6. ለሎት 5 የታደሰ የሶስተኛ ወገን የመድን ምስክር ወረቀት፣ሊብሬ ኮፒ በማካተት ጨረታ ማስከበሪያ 5000.00(አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት (CPO) እንዲሁም ከላይ ከተራ ቁጥር 6 ያለውን ተከኒካል ሰነድ ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ለእቃ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን እቃ 2% ጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡
  8. ተጫራቾች የተሟላ በአማርኛ የተዘጋጀ ሰነድ ለያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 150.00 ብር አንድ መቶ ሃምሳ ብር ከፍለው ከጽ/ቤታችን ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ፡፡
  9.  ተጫራቾች ከጨረታ መክፈቻ ቀን በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙናውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡ናሙና ባላቀረቡባቸው እቃዎች ዋጋ መወዳደር አይቻልም፡፡ናሙናው እስከ 6ወር ካልተረከቡ ተወርሶ በንብረትነት ይመዘገባል፡
  10. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት የሚወዳደሩበትን ፋይናንሻያል(ዋጋ) ኦሪጅናልና ኮፒውን እና ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 11 የስራ ቀናት ከ11ኛው ቀን እስከ 4፡00 ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11.  ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት የስራ ቀናት በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  12. የጨረታው መከፈቻ ከኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ (አስቸኳይ ስብሰባ) ካጋጠመ በማስታወቂያ በማሳወቅ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  13.  ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14.  በዚሁ የጨረታ መመሪያ ያልተካተቱ ሌሎች ሁኔታዎች በአገሪቱ ሕግና ደንብ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት የሚታይ ይሆናል፡፡

አድራሻ፡- ሀይሌ ጋርመንት ን/ስ/ላ/ክ/ከ/ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሲሆን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-10275863/09-40327450 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ወይም በአካል ቅ/ፅ/ቤቱ ድረስ በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-10
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት የስራ ቀናት በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-10 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት የስራ ቀናት በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nifas SIlk Lafto Sub City Land Development & Management Agency
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 150.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 29, 2026)
  • Posted at: 2026-10-29T11:01:11.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders