Stationery
የቦንጋ እጸዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና ማቆሚያ ሼድ እና የቦቃ ዘረመል ፍተሻ ጣቢያ አጥር ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸምና ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 01/2019
የቦንጋ እጸዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ፤ የመኪና ማቆሚያ ሼድ እና የቦቃ ዘረመል ፍተሻ ጣቢያ አጥር ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸምና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 01 የጽህፈት መሳሪያ ግዥ
- ሎት 02 ለቢሮ ሠራተኞች የደንብ ልብስ ግዥ
- ሎት 03 መኪና ጎማ ግዥ(የሎንግ ቤዝና የፎርድ መኪና)
- ሎት 04 የመኪና ማቆሚያ ሼድ ግንባታ
- ሎት 05 የዘር ጥራት ፍተሻ (GOT) ጣቢያ አጥር ግንባታ
በዚሁ መሠረት
1. በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
2. ህጋዊ የኮንስትራክሽን የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ እንዲሁም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
3. የዘመኑን ግብር የከፈለበትና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
5. የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (Tin no) ያላቸው፤
6. በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
7. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 01 እና 02 ብር 4000፤ ለሎት 03 ብር 5000፤ ለሎት 04 እና 05 ብር 10000 በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሎት 01፤02 እና ለሎት 03 ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት እንዲሁም ለሎት 04 እና 05፤ 21 ተከታታይ ቀናት ዘወትር የስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100(አንድ መቶ) ብር ብቻ በማዕከሉ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000099955361 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነድ ከማዕከሉ ግዥ ክፍል መውሰድ ይችላል።
8. ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለት 15 ተከታታይ ቀናት የግዥን እንዲሁም ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት የመኪና ማቆሚያ ሼድ እና የዘር ጥራት ፍተሻ ጣቢያ አጥር ግንባታ እና የመኪና ጥገና የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዳቸውን ዋናና ኮፒ ለየብቻ ተፈላጊ መረጃዎች ጋር በፖስታ በማሸግ በቦንጋ እፅ/ዘር/ጥ/ቁ/ማዕከል የግዥና ክፍያ ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖረባቸዋል።
9. የመኪና ማቆሚያ ሼድ እና የቦቃ ዘረመል ፍተሻ ጣቢያ አጥር ግንባታ ተጫራቾች ቴክኒካና ፋይናንሻል ሰነድ ሲመልሱ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት ማንኛውም መረጃ ላይ ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል።
11. ጨረታው ለግዥዎች በ16ኛው ቀን የመኪና ማቆሚያ ሼድ እና ዘረመል ፍተሻ ጣቢያ አጥር ግንባታ በ22ኛው ቀን ከሰዓት 8:30 ታሽጎ በዕለቱ በ9:00 ሰዓት ተጫራቾችውም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ የተጠቀሰው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
12. በጨረታ ሰነድ ላይ ማብራሪያ የሚፈልግ ማንኛው ተጫራች ማብራሪያ መጠየቅ የሚችለው ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ(10) ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
13. ውጤት አስመልክቶ ቅሬታ ማቅረብ የሚቻለው የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለሰባት (07) ተከታታይ ቀናት ብቻ ነው
14. የመኪና ማቆሚያ ሼድ እና የቦቃ ዘረመል ፍተሻ ጣቢያ አጥር ግንባታ አሸናፊው ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት ውል ማስከበሪያ (performance bond) ለማስያዝ ፍቃደኛ መሆን አለበት፡፡
15. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ተጫራቾች ለሚያቀርቡ ዕቃ ናሙና ( ሳምፕል) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
16. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርቦ ውል በመግባት የሚያቀርባቸውን ዕቃዎች እስከ ማዕከሉ ግቢ ድረስ ማቅረብ አለበት። ይህ ሳይሆን በውሉ መሠረት ዕቃዎች ባይቀርቡ ስራው ቢስተጓጎል በግዥ ኤጀንሲ ደንብ ወይንም በኮንስትራክሺን ህግ መሠረት ውል ተቀባይ እንዲጠየቅ ይደረጋል፡፡
17. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ነገር ግን በእያንዳንዱ ሎት ላይ የተካተቱ ሀሳቦች በጋዜጣ እንደወጣ ይቆጠራል፡፡
18. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0936 725 132 / 0910 215 680 ደውለው ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
የቦንጋ እጸዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-11-20
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-11-20 15:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Bonga Plant Seed Quality Control and Testing Center
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 30, 2026)
- Posted at: 2026-10-30T07:09:37.000Z
- Source: Qelal Tenders