Equipment and Accessories
በደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ አገልገሎት የሚውል እቃዎች መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ወሎ ዞን የተህለደራ ወረዳ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ አገልገሎት የሚውል አላቂ የጽህፈት መሳሪያ ሎት1 ቋማ እቃ ሎት 2 ህትመት ሎት 3 የጽዳት እቃዎች ሎት 4 የሰራተኞች ደንብ ልብስ እና ጫማ ሎት 5 በግልጽ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል።
1. የዘመኑ የታደሰ ንግደ ስራ ፈቃድ ያላቸው
2. በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ተከታታይ የደረሰኝ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ
3. የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው
4. የገዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ / ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ አለባቸው። ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከተሁ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ የስራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ለሚወዳደሩበት ወይም የዕቃ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተሁ/ወ/ፍ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ውስጥ ከቀኑ 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 - በ16ኛው ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልከ ቁጥር 09 39 00 51 65 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ፍርድ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-13
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀን ውስጥ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-14 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: South Wollo Zone Tehuldere Woreda Court
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 30, 2026)
- Posted at: 2026-10-30T07:12:36.000Z
- Source: Qelal Tenders