Vehicle and Machinery Sale
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ገልባጭ የደረቅ ጭነት መኪና፣ የሰው እና የደረቅ ጭነት መኪና ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የተጫራቾች መመሪያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መኪኖች በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ፡-
- ሎት አንድ፡- ገልባጭ የደረቅ ጭነት መኪና
- ሎት ሁለት፡- የሰው እና የደረቅ ጭነት መኪና ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት የጨረታ ተሳታፊ መሆን የሚፈልጉ ማንኛውም ተወዳዳሪ መወደደር እንዲችሉ ፤
1. ተጫራቾች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመቅረብ ለሁለቱም ሎቶች ለየብቻ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 09/03/2019 ዓ.ም ቀን ድረስ በጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ጅዳ ወረዳ አስተዳደር ግቢ ውስጥ በአካል በመገኘት የመኪኖቹን ይዘት በማየት የሚወዳደሩበትን የብር መጠን በመሙላት ማስገባት አለባቸው።
3. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ እና የጨረታ ማስከበሪያ CPO ለብቻ በማሸግ እነዚህን 3 ዶክመንቶች በአንድ ፖስታ (mother envelope) በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።በተጨማሪ እያንዳንዳቸዉ ዶክመንት ላይ ኦርጂናል፤ ኮፒ እንዲሁም CPO በማለት በፖስታው ላይ መጻፍ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ እስከ 10/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በዚሁ እለት ማለትም በ10/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል ይሁን እንጂ ተወዳዳሪዎች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ህጋዊ የጨረታ ኮሚቴዎች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
6.ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ ካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ የተወዳደሩበትን ጠቅላላ የብር መጠን 1/4 ለጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ብሎ ለሁለቱም ሎቶች ለየብቻ በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ከጨረታ መክፈቻው ቀን እና ሰዓት በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
8. አሸናፊው ተወዳዳሪ ያሸነፈበትን የብር መጠን ሙሉ በሙሉ በመ/ቤቱ አካውንት ላይ ካስገባ ለጨረታ ማስከበሪያ ካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ተይዞ የነበረዉ ይመለስለታል።
9. ለተሸናፊ ተወዳዳሪዎች አሸናፊው ተወዳዳሪ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ አስይዞ የነበረው ካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ የሚመለስ ይሆናል።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ ፡- ከአ/አ ላምበረት መነሀሪያ ጅዳ/ስርጢ ብለዉ በጣፎ አርባራት መንገድ ተሳፍሮ መምጣት ይችላሉ።
- ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሰው ስ.ቁ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ስልክ ቁጥር፡-011-673 6328
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-19
- Bid closing time: 09:00
- Bid opening: 2026-11-19 09:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Jedda Wereda F/E/D/B
- Bid bond: 25%
- Bid document price: 500.00 ብር በየሎቱ
- Published on: Addis Zemen (Oct 30, 2026)
- Posted at: 2026-10-30T07:28:10.000Z
- Source: Qelal Tenders