Equipment and Accessories
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት (አዲስ አበባ) ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የአቅርቦት እና ገጠማ ሥራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥሮች DCE/SF/141/2026 እና DC/SF/142/2026
የመከላከያ ኮንስትራክሸን ኢንተርፕራይዝ ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት (አዲስ አበባ) ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሠንጠረዥ በዝርዝር የተጠቀሱትን የተለያዩ የአቅርቦት እና ገጠማ ሥራዎች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃውን አይነት |
የፕሮጀክት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ
|
|
1 |
Supply & fix Alarm system |
ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት (አ/አ) |
DCE/ SF/141/2026 |
ኅዳር 02/ 2019 ዓ.ም 4፡15 ሰዓት |
ኅዳር 02/2019 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት
|
50,000.00 |
|
2 |
Supply of Light Fitting and Distribution board |
ለፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት (አ/አ) |
DCE/SF/142/2026 |
ኅዳር 02/2019 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት |
ኅዳር 02/2019 ዓ.ም 4፡45 ሰዓት
|
50,000.00 |
ስለሆነም፡-
1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ…ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ (Bid Bond) 120 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ለእያንዳንዱ ጨረታ ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) መቅረብ ይኖርባቸዋል። የመድን ድርጅቶች ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለያንዳንዱ ጨረታ ቁጥር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት አዲሱ ቢሮ ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ ውስጥ
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0911171751/0913297297
E-mail አድራሻ [email protected]
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-11-11
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-11-11 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
- Buyer's registered address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
- Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Oct 30, 2026)
- Posted at: 2026-10-30T07:44:35.000Z
- Source: Qelal Tenders