Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በጉለሌ ክ/ከተማ የወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

  • ሎት 1 አላቂ የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 70000.00 (ሰባ ሺህ ብር)
  • ሎት2 አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የፅህፈት መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 56,000.00 (ሃምሳ ስድስት ሺህ ብር)
  • ሎት 3 የደንብ ልብስ ጨረታ ማስከበሪያ 80,000.00 ( ሰማንያ ሺህ ብር)
  • ሎት4 የተሽከርካሪ ጎማ የመኪና ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር)
  • ሎት 5 የደንብ ልብስ ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር)
  • ሎት 6 የኮምፒውተር ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና ጨረታ ማስከበሪያ 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
  • ሎት 7 የዲኮር ኪራይ ስራ ጨረታ ማስከበሪያ 5,000.00( አምስት ሺህ ብር)

በጨረታው ለመካፈል ተጫራቾች

1ኛ በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በስማቸው ያላቸው የዘመኑን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርቡ።

2ኛ ተጫራቾች የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN NUMBER/VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ወይም ቲኦቲ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልጋል።

3ኛ ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ከፋይናንስ ፅ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።

4ኛ ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ኦሪጂናል ሰነድ እና ፎቶ ኮፒ ሰነድ በተናጠል ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱን ስም ማህተም ስልክ ቁጥር እና ፊርማ መኖር አለበት። የሚጫረቱበትን እቃ አይነት በመጥቀስ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 የሥራ ቀናት በስራ ሰአት በቢሮ ቁትር 14 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5ኛ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ባበቃ በመጨረሻው ቀን 10፡30 ሰዓት ይታሸግና በማግስቱ 3፡00 ሰአት ይከፈታል።

6ኛ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ/CPO/ ማስያዝ አለባቸው እና የጨረታው አሸናፊ 10% የጨረታውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7ኛ አሸናፊው ተጫራች ዘወትር በስራ ሰአት 2፡30 እስከ 11፡30 ንብረቶችን በራሱ በማጓጓዝ ማስጫኛውን እና ማውረጃውን ጨምሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ማውረድ ይኖርባቸዋል።

8ኛ ፅ/ቤቱ የሚያጫርተውን እቃ ብዛት 20% መቀነስ መጨመር ይችላል።

9ኛ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በሙሉም ሆነ መከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ለተጫራቾች ማብራሪያ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 011 122 6704 እና 011-801 202-4004 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

10ኛ ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበትን እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው ናሙና ማቅረብ የማይችሉ ከሆነ ገላጭ እስፔስፍኬሽን ማምጣት አልያም እቃውን የሚያሳይ ጥራት ያለው ፎቶ ማምጣት ይኖርበታል።

11ኛ ማንኛውም ተጫራች የመንግስት ግዥ አቅራቢነት ዝርዝር (SUPPLIER LIST) የተመዘገበ ሆኖ የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡።

አድራሻ፤- ሽሮ ሜዳ ከስላሴ ቤተክርስቲያን በታች ባለው በግራ በኩል መታጠፊያ 500 ሜትር ገባ ብሎ።

በጉለሌ ክ/ከተማ የወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-10
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 የሥራ ቀናት ቆይቶ በመጨረሻው ቀን 10፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-11 09:00
  • Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 የሥራ ቀናት ቆይቶ በማግስቱ 3፡00 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gulele Sub City Woreda 6 Finance Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 30, 2026)
  • Posted at: 2026-10-30T07:48:43.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders