Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ የእስቴሽነሪ እና የጽዳት እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Cleaning and Janitorial Equipment and ServiceStationeryOffice Supplies and Services
Central Ethiopia
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ
- የእስቴሽነሪ፣
- የጽዳት እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- በየዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/ በባንክ ተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ ግዢና ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ድርጅቶች የተጨማሪ እሴት ታክስን በማካተት በሰም በታሸገ ኤቨሎፕ (ፖስታ) በማሸግ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሰት የፍትህ ቢሮ ግዢና ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬትቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሳጥን በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046556250 በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በማእ ኢት/ ክልላዊ መን/ የፍትህ ቢሮ ግዥ; ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
Tender details
- Deadline: 2026-11-11
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-11 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Central Ethiopia Regional State Justice Bureau
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 30, 2026)
- Posted at: 2026-10-30T08:10:09.000Z
- Source: Qelal Tenders