Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ/ም ለተቋሙ የሚያስፈልጉ የደንብ ልብሶች (1)፣ የጽዳት እቃዎች (2)፣ የተለያዩ የጽህፈት እቃዎች (3)፣ እድሳት እና ጥገና (4)፣ ህትመት (5)፣ ቋሚ እቃ (6) እና የእድሳት እቃዎችን (7) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በቂ/ክ/ከ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ/ም ለተቋሙ የሚያስፈልጉ፡

  1. የደንብ ልብሶች
  2. የጽዳት እቃዎች
  3. የተለያዩ የጽህፈት እቃዎች
  4. እድሳት እና ጥገና
  5. ህትመት
  6. ቋሚ እቃ
  7. እድሳት እቃዎች። በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች ሟሟላት የሚችል ማንኛውም ህጋዊ የንግድ ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው ቅጥር ጊቢ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 በስራ ሰአት በመቅረብ እና በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሀምሳ ብር ብቻ) በመክፈል እና የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ በመውሰድ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታው በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ11፡30 ተዘግቶ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች:-

1. በግብር ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ መያዣ የሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% (ፐርሰንት) በጤና ጣቢያው ስም በተዘጋጀ ሲፒኦ (CPO) ኮፒው ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት አስፈላጊውን የትብብር ደብዳቤ ለማወዳደር የሚከፈተው ፖስታ ማለትም በኮፒው ውስጥ በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።

5. አሸናፊው የንግድ ድርጅት የጠቅላላ ዋጋውን 10% በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅበታል።

6. ኦርጅናል ፖስታ በጨረታ ማወዳደሪያ ወቅት አይከፈትም።

7. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ድረገጽ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዝርዝር ጤና ጣቢያው ባቀረበው የዋጋ ሰንጠረዥ ላይ በመሙላት እና እያንዳዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋጋውን እና ኮፒውን በታሽገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም ቴክኒካል ሰነድ ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ በድጋሚ በአንድ ፖስታ መታሸግ አለበት።

9. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ሁሉም ተጫራቾች ናሙና ከጨረታው ሰነድ በጋራ ማቅረብ አለባቸው።

10. ለጨረታ የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።

11. ማንኛውም ተጫራች መወዳደር የሚችለው ከንግድ ፈቃድ ጋር ተያያዥነት ባላቸው አቅርቦቶች አገልግሎቶች ላይ ብቻ ነው።

ማሳሰቢያ፡- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን ሙሉበሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የሚቀርቡት ዋጋዎች ተጨማሪ እሴት ታክስን/ተርን ኦቨር ታክስን ያካተቱ መሆን አለባቸው።

ከገነት ሆቴል ወደ ሽመልስ ሀብቴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሚያስገባው መንግድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር /0115 53 64 56/0115 1561 92 በመደወል መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን

በቂ/ክ/ከ/የቂርቆስ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-11
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-12 10:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kirkos Sub City Health Bureau Kirkos Health Post
  • Buyer's registered address: ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ከገነት ሆቴል ወደ ሽመልስ ሀብቴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ነው
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 250.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 31, 2026)
  • Posted at: 2026-10-31T08:29:02.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders