Tri Wheeler, Motorcycles and Bicycles Purchase
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ዉሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ሞተር ሳይክል ዕቃ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Tri Wheeler, Motorcycles and Bicycles PurchaseSpare Parts and Car Decoration MaterialsSouth West Ethiopia Region
Description
ሞተር ሳይክል ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ውሃ /ዕቃ/ግ/ጨ/ቁ-004/2019
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ዉሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ሞተር ሳይክል ዕቃ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ሞተር ሳይክል አቅራቢነት ዘርፍ የተሰማሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ፣ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት፣ የቲን/tin/ እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክሜንት ሊገዙ ሲመጡ ኦርጅናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር / በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝ/ክል/መ/ዉሃ/ማዕ/ኢነ/ ቢሮ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000454343507 ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሰነዱን መዉሰድ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CP.O/ ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተገደበ ቢድ ቦንድ / unconditional Bid Bond/ለ(90) የስራ ቀናት የሚቆይ 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝ/ክል/መ/ዉሃ ማዕ/ኢነ/ቢሮ ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማዘጋጀት አንድ(1) ኦርጅናልና ሁለት(2) ኮፒ በተለያዬ ፖስታ ታሽጎ ፖስታው ላይ ኦርጅናልና ኮፒ የሚል ጽሑፍ ተለይተው መቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በእያንዳንዱ ሞተር ሳይክል ዓይነት በገዙት ኦሪጂናል ሰነድ ላይ ባለው ሰንጠረዥ ከነቫት በመጻፍ በሰም/በሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝ/ክል/መ/ዉሃ/ማዕ/ኢነ/ ቢሮ / ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያዉ ዕለት ከሰዓት 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝ/ክል/መ/ዉሃማዕ/ኢነ/ ቢሮ ይከፈታል።
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ከላይ በተገለጸው መሰረት ይሆናል። በመክፈቻው ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መከፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
- አሸናፊ ተጫራች ሞተር ሳይክል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝ/ክል/መ/ውሃ ማዕ/ኢነ/ ቢሮ ድረስ በማምጣትና በማስፈተሽና የማስረከብ ግዴታ አለበት።
- ቢሮ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ 047 331 2551 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የውኃ፣
ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ /ቦንጋ/
Tender details
- Deadline: 2026-11-16
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-16 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 31, 2026)
- Posted at: 2026-10-31T08:36:18.000Z
- Source: Qelal Tenders