Others
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በሆስፒታሊቲ ዘርፍ ከሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነው ገነት ሆቴል አስተዳደር በሆቴሉ ግቢ ውስጥ ያሉትን ክፍት ቦታዎች ለሕፃናት መጫወቻ የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራ ወይም የተለያዩ ከሆቴሉ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ኢቨንቶች ለሚያዘጋጁ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
የልጆች መጫዎቻ ስፍራ እና የስፖርት ማዝወተሪያ ቦታ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በሆስፒታሊቲ ዘርፍ ከሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነው ገነት ሆቴል አስተዳደር በሆቴሉ ግቢ ውስጥ ያሉትን ክፍት ቦታዎች ለሕፃናት መጫወቻ የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራ ወይም የተለያዩ ከሆቴሉ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ኢቨንቶች ለሚያዘጋጁ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ቦታውን በራሳቸው ወጪ በማልማት መከራየት ይችላሉ።
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት (VAT) ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ ምዝገባና ሰርተፍኬትና መለያ ቁጥር (TIN) ሰነድ ያላቸው፤
- ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ታሳቢ የሚደርግ 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ከድርጅታችን የፋይናንስ ክፍል የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና ለገነት ሆቴል” በሚል በማሠራት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ቦታውን በአካል ተገኝተው በማየት 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ እና 10% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ በጥቅል ቦታውን በወር የሚከራዩበትን ዋጋ በመግለጽ ቴክኒካል መስፈርቱንና ፋይናንሱን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ, ገነት ሆቴል አስተዳደር ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን እስከ አሥረኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ አስተዳደር ክፍል ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፣ አስረኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ጨረታው ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻችው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- አንድ ተጫራች መጫረት የሚችለው በአንድ የጨረታ ሰነድ ብቻ ነው።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አ/አ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ካሳ ግራንድ ሞል ፊት ለፊት
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- 011 550 4701 / 09 11-25 06 41 / 09 39-50 00 00
በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሠልጠኛ ኢኒስቲትዩት የገነት ሆቴል
Tender details
- Deadline: 2026-11-09
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-09 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Genet Hotel Administration
- Buyer's registered address: አ/አ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ላይ ገነት ሆቴል ግቢ ውስጥ
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 31, 2026)
- Posted at: 2026-10-31T09:01:22.000Z
- Source: Qelal Tenders