Others

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የገነት ሆቴል አስተዳደር በሆቴሉ ግቢ ውስጥ ያለውን ቦታ ለሕፃናት መጫወቻ ወይም የተለያዩ ከሆቴሉ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ኢቨንቶች ለሚያዘጋጁ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

Description

የቦታ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የገነት ሆቴል አስተዳደር በሆቴሉ ግቢ ውስጥ ያለውን ቦታ ለሕፃናት መጫወቻ ወይም የተለያዩ ከሆቴሉ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ኢቨንቶች ለሚያዘጋጁ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡-

በመሆኑም

  • የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት (VAT) ያላቸው፤
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያለው

ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፡-

  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 ( አምስት ሺህ ብር ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለገነት ሆቴል በሚል በማሠራት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  • የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከድርጅታችን አስተዳደር ክፍል የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
  • ተጫራቾች ቦታውን በአካል ተገኝተው በማየት 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ እና 10% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ በጥቅል ቦታውን በወር የሚከራዩበትን ዋጋ በመግለጽ ቴክኒካል መስፈርቱንና ፋይናንሱን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ገነት ሆቴል አስተዳደር ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን እስከ አሥረኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ አስተዳደር ክፍል ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፣ አስረኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ጨረታው ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻችው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  • አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
  • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ 09 39-50-00-00

በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሠልጠኛ ኢኒስቲትዩት የገነት ሆቴል


Tender details

  • Deadline: 2026-11-14
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ገነት ሆቴል አስተዳደር ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን እስከ አሥረኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-14 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ገነት ሆቴል አስተዳደር ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን እስከ አሥረኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Genet Hotel Administration
  • Buyer's registered address: አ/አ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ላይ ገነት ሆቴል ግቢ ውስጥ
  • Bid bond: 5,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 31, 2026)
  • Posted at: 2026-10-31T09:03:43.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders