Textile, Garment and Leather
በአዲስ አስባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለሚጠቀምባቸው የእቃና አገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
More tags
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ 01/2019
በአዲስ አስባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለሚጠቀምባቸው የእቃና አገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት 1 የደንብ ልብስ
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እታዎች
- ሎት 3 የፅዳት እቃዎች
- ሎት 4 ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 5 ለእንስሳት ህክምና የሚያገለግሉ አላቂ ዕቃዎችና መድሀኒቶች
- ሎት 6 የላብራቶሪ ዕቃዎችና ኬሚካሎች
- ሎት 7 የግብርና የደን እና የባህር ግብአቶች እና እቃዎች
- ሎት 8 የአካል ጉዳተኛ እቃዎች
- ሎት 91 የተሽከርካሪ መኪና የወንበር ልብስ፣ መፍቻዎች፤ ሽቶዎችና ጌጣጌጦች
- ሎት 10 የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት
- ሎት 11 የህትመት ሥራዎች
- ሎት 12 የመስተንግዶ ግዥ
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥና የፋይናንስ መመሪያዎች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ሎት/ምድብ በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (የተመዘገበበት ቀን አቅራቢነቱ ከመስኩ ጋር የሚመሳሰል ባለቤትነት የሚገልፅ) የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ መቅረብ ይኖርበታል።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች በገቢዎች ሚኒስቴር በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ጊዜው ያላለፈበት የድጋፍ መረጃ /ክሊራንስ/ማያያዝ ይኖርዝቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 በመቅረብ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጨረታውም በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ በኮሚሽኑ የስብሰባ አዳራሽ 7ተኛ ፎቅ /ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል ነገር ግን ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ከሆነ, በሚቀጥለው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በስፔስፊኬሽኑ መሰረት ብቻ ሞልተው በየሰነዳችሁ ኮፒ ላይ በመፈረም የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ፣ ፋይናንሻል አርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው 4 ፖስታ በማሸግ ፖስታው ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በደንብ አሽገው ኤንቨሎፕ ላይ ኮፒና ዋና ሰነድ ብለው በመለየት የግዥ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. በአንድ ምድብ የምትጫረቱ ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ምድብ ፖስታው ላይ በመግለፅ የተጫረቱበት ምድብ /ሎት 5000 (አምስት ሺህ) ብር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሌሎችህጋዊ ሰነዶች ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. ከአንድ በላይ በሆነ ሎት /ምድብ የምትጫረቱ ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ሎት/ምድብ በመግለፅ ለየብቻ በማሸግ ሁሉንም በአንድ ፖስታ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባችኋል ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ሎት ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ከ5,000 (አምስት ሺህ ብር) ሲፒኦ በማሰራት ለሎቱ በተዘጋጀው ኦሪጅናል ሰነድ የያዘ ፖስታ ውስጥ በማስገባት የሎት ቁጥር መጠሪያ በፖስታ ጀርባ ላይ በመፃፍ ማቅረብይጠበቅባቸዋል።
10. በሎት/ምድብ 1፣ 2፣3፣9 ለተጠቀሱት እቃዎች ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ የእቃዎቹን ናሙና አብረው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
11. በሎት/ምድብ 4፣5 እና 6፣ 7፣ 8፣ 11፣ 12 ላይ ለወጡ እቃዎች ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ኮሚሽኑ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት የሚያቀርቡ ሲሆን እቃዎቹም ለኮሚሽኑ ከቀረቡ በኋላ በኮሚሽኑ የጥራት ኮሚቴ ጠያቂው የስራ ክፍል ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት መሆኑን አረጋግጦ የሚረከብ ይሆናል።
12. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች ካደራጃቸው ተቋም የጨረታ ሰነድ በነፃ እንዲወስዱና ለጨረታ ማስከበሪያ እንደሚያገለግል የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
13. ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
14. ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን እዚህ ላይ ያልተገለፁ በሰነዱና በግዥ መመሪያው መሰረት የሚስተናገድ ይሆናል።
15. ተጫራቾች ተቋሙ ካቀረበው ስፔስፊኬሽን ውጪ ሌላ ስፔስፊኬሽን መጨመር መቀነስ ወይም ሰርዞ ማስተካከያ ማድረግ የተከለከለ ነው።
16. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ አ/አ/ከ/ግ/ል/ከ 22 መክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ያሬድ ኢንጅነሪንግ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403
ስልክ ቁጥር 011 1659-0983
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን
Tender details
- Deadline: 2026-11-10
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-11 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Urban Agriculture and Farmers Development Commission
- Bid bond: ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ከ5,000 (አምስት ሺህ ብር)
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 01, 2026)
- Posted at: 2026-11-02T08:50:30.000Z
- Source: Qelal Tenders