Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ
- ደንብ ልብስ (6211)
- አላቂ የቢሮ እቃዎች (6212)
- ህትመት (6213)
- አላቂ የፅዳት ዕቃዎች (6218)
- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች (6219)
- ለማሽነሪ እና ለፕላንት ጥገና (6243)
- ለፕላንት እና ማሽነሪ መሳሪያ መግዣ (ቋሚ እቃዎች) (6313)
- አላቂ የህክምና እቃዎች (መድኃኒትና ሪጀንቶች) (6214)
- ለህንፃ እና ቁሳቁስ ተገጣጣሚዎች ጥገና (የግንባታ እና ፓርቲሽን ስራዎች) (6244)
- ለጭነት አገልግሎት ትራንስፖርት (6255)
- ለመስተንግዶ (ለጤና ተቋሙ ካፍቴሪያ) (6233)
- የሮቶ እጥበት እና ጥገና (6245) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰቦች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው ሆኖ የዘመኑ ግብር የገበረ ከገቢዎች በአቅራቢነት የተመዘገ በማስረጃ ማቅረብ አለበት። ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ እና በአቅራቢነት የተመዘገበ በማስረጃ ማቅረብ አለበት።
1. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ።
2. ማንኛውም ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የእቃ አይነት ጠቅላላ ዋጋ እና የአንዱን ዋጋ ከፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ በሰጠው ፎርም ላይ መሙላት ይኖርበታል። የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የነጠላ ዋጋ ይወሰዳል።
3. ተጫራቾች ጨረታውን በትክክል በታሸገ እና ሙሉ አድራሻው በትክክል በታወቀ ኤንቭሎፕ በሁለት ፖስታ በማድረግ ከላያቸው ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ ብለው መፃፍ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ያቀረቡት CPO ኮፒ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ወይም ዋስትና ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቾች ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የእቃዎቹን መስፈርቶች አይነት ሳይለወጡና ሳይነካኩ በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት (ፎርም) ላይ በትክክል ሞልተው ማቅረብ እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በጤና ጣቢያው ቢሮ ቁጥር 40 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች የሚያቀርባቸውን እቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት። ለጨረታው የቀረበው ሰነድ ላይ ሰርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በአጋጣሚ ቢሳሳትና ቢስተካከል በቦታው ፊርማ ሊኖረው ይገባል።
7. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት በፍፁም አይቻልም።
8. ተጫራቾች ጨረታውን በትክክል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዳቸው ከታች በተ.ቁ 1፣2፣3፣4፡5፡6፣10፣11 እና 12 ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ለተ.ቁ 7 እና 8 ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) ለተ.ቁ 9 CPO ማቅረብ ይኖርበታል።
10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 እና ከሰዓት 7፡30-11:30 ሰዓት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ መለስተኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም የጨረታውሂደት አይሰረዝም።
11. መስሪያ ቤቱ አሸናፊው ድርጅት እንደታወቀ የጨረታውን ውጤት ወዲያውኑ ያሳውቃል።
12. ማሳሰቢያ፡- ኦርጂናል ፖስታዎች በጨረታ መክፈቻ እና መወዳደሪያ ወቅት የማይከፈት መሆኑን እንገልፃለን። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. አድራሻ፡- በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ የሚገኝበት ቦታ ቡልጋሪያ አለፍ ብሎ ከኖክ ማደያ በስተግራ ታጥፎ በሚወስደው መንገድ 150 ሜትር ገባ ብሎ ከሰኒ ሳይድ ት/ቤት ጀርባ ወይም ከኢንትርናሸናል ክሊኒካል ላብራቶሪ ዝቅ ብሎ ይገኛል።
14. ስልክ ቁጥር 011 4 62 49 47 የወ/ት የሚ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-11-13
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-13 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Feres Meda Health Post
- Buyer's registered address: በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ የሚገኝበት ቦታ ቡልጋሪያ አለፍ ብሎ ከኖክ ማደያ በስተግራ ታጥፎ በሚወስደው መንገድ 150 ሜትር ገባ ብሎ ከሰኒ ሳይድ ት/ቤት ጀርባ ነው፡፡
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 01, 2026)
- Posted at: 2026-11-02T09:21:25.000Z
- Source: Qelal Tenders