Equipment and Accessories
በሰሜን ጎጃም ዞን የዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Amhara
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሰሜን ጎጃም ዞን የዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ለሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ
- ሎት 1. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና
- ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርት አሟልተዉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ የእቃው ግዥ መጠን ከብር 500,000 (ከአምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀቶችን ከዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (ለአስር) ተከታታይ ቀናት ድረስ በዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን በአካል በመቅረብ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመስሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የዋጋ ማቅረቢያና አስፈላጊ ሰነዶችን ኮፒ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅት ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ባይገኙም በጽ/ቤቱ የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን መክፈቻ ቀኑ ማለትም በ11ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ለሎት 1. ብር 30,000 እና ለሎት 2. ብር 10,000 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በሎት ድምር ዋጋ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች በመጫረቻ ሰነዱ የተዘረዘረውን ሎት ሁሉንም ዝርዝር ሥርዝ ድልዝ ሳያደርግ ያንዱን ዋጋ ጠ/ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በራሱ ወጭ ዱርቤቴ ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- ይህ የግዥ ጨረታ በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱትን ጉዳዮችን በአብክመ የግዥ መመሪያ 144/18 መሰረት የሚመራ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች /አገልግሎቶች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን)፣ መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለበለጠ መረጃ ዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ግዥ ፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 223 08 16 /09 74 50 58 99 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-12
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-12 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: ዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
- Published on: Be'kur (Nov 02, 2026)
- Posted at: 2026-11-03T11:20:45.000Z
- Source: Qelal Tenders