Stationery
በምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የወምበርማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት ለወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች /እስቴሽነሪ/ (ሎት 1) እና የፕሪንትር ቀለሞች (ሎት 2) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የወምበርማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት ለወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች /እስቴሽነሪ/ እንዲሁም
- ሎት 2. የፕሪንትር ቀለሞች ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መግዛትና ማስቀረብ ይፈልጋል፡፡
በዚህ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች በግብር ዓመቱ የታክስና የግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ወይም (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታከስ ወይም (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ በመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተዘረዘሩትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ሰነድ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 ተከታታይ ቀን እስከ 11፡30 ድረስ የማይመስስ ብር ለአንድ ሰነድ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መገዛትና መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጨረታ ብር ለሎት 1. ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) እንዲሁም ለሎት 2. ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሞሉት የዋጋ ዝርዝር ላይ የድርጅቱ ማህተም፣ ስም፣ ፊርማ እንዲሁም ቀን በመፃፍ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀን እስከ 11፡30 የሚውል ሲሆን ጨረታው 11ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሳጥኑ ታሽጎ ሎት 1. ከረፋዱ 4፡30 እንዲሁም ሎት 2. ከረፋዱ 5፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት የማያግደን ከመሆኑም በተጨማሪ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ በትክክል ለመሙላታቸው በማረጋገጥ የተሞላውን ዋጋ ኮፒ በማድረግ ኦርጅናል ሰነዱን በአንድ ፖስታ ኮፒውን በአንድ ፖስታ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ለወምበርማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ተብሎ በማሰራት በራሱ አንድ ፖስታ በማድረግ እነዚህን 3 /ሶስት/ ፖስታዎች ማለትም ኦርጅናል ኮፒና ሲፒኦ በአንድ ፖስታ በማድረግ ፖስታው ላይ የተጫራቹን ስም፣ ፊርማ እና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ለወምበርማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በማለት መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ግዥ ፈፃሚ መስሪያ ቤቱ የሚፈጸሙ ገዥዎችን 20 በመቶ መጨመር እና መቀነስ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን አቅርቦቶች ወምበርማ ወረዳ ድረስ በራሳቸው ወጭ አጓጉዘው በማምጣት በወረዳው ባሉ ሴክተር መ/ቤቶች ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ እንዳለባቸው ታሳቢ በማድረግ በመሙላት መወዳደር አለባቸው፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራቾ አሸናፊነቱ በተገለፀ በ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ወምበርማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በሲፒኦ በማሰራት ውል መያዝ አለበት፡፡ በዚህ በተገለፀው ቀን ውስጥ መጥቶ ውል መያዝ ባይችል በግዥ መመሪያው ቁጥር 144/2018 መሰረት እርምጃ የምንወስድ መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በየሎት ድምር ስለሆነ በሚወዳደሩበት ሎት በከፊል መሙላት ከውድድር ውጭ ይፈልጋል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉትን የመወዳደሪያ የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ መሙላት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተካተቱ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወምበርማ ወረዳ ገንዘብ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 449 02 15 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወምበርማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-12
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀን እስከ 11፡30 የሚውል ሲሆን ጨረታው 11ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00
- Bid opening: 2026-11-12 11:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Amhara
- Publishing entity: Womeberma Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Be'kur (Nov 02, 2026)
- Posted at: 2026-11-03T12:08:07.000Z
- Source: Qelal Tenders