Freight Transport

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2018/19 ምርት ዘመን በተለያዩ ቦታዎች ላይ ያስመረተውን ምርጥ ዘርና የምግብ እህል በጨረታ አወዳድሮ ወደ ባሕር ዳር ወይም ወረታ ማጓጓዝ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ባምዘማ/ሽ 18/2019

በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት በ2018/19 ምርት ዘመን በተለያዩ ቦታዎች ላይ ያስመረተውን ምርጥ ዘርና የምግብ እህል በጨረታ አወዳድሮ ወደ ባሕር ዳር ወይም ወረታ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1.  በዘርፉ የታደሰ የንግድ ዘርፍ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ስለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ከመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን የምዝገባ ፈቃድና በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት የተረጋገጠ የተሸከርካሪዎች ዝርዝር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚጓጓዘው ምርጥ ዘርና የምግብ እህል ብዛት እንደየቦታው የሚለያይ ሆኖ ለአንድ ኩንታል የሚያጓጉዝበትን ዋጋ በመሙላት መቅረብ አለባቸው፡፡ ዝርዝር መጠኑ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት መጠን የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በባሕር ዳር ቅርንጫፍ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በፖስታ በማሸግ በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ህዳር 3/2019 ዓ.ም ለቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ይከፈታል፡፡
  11.  ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12.  ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 78 74 49 59 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ አድራሻ ባ/ዳር ቀበሌ 16 ጉደር ዱቄት ፋብሪካ በስተጀርባ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች
ኮርፖሬሽን የባሕር ዳር
ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-12
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-11-12 14:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Ethiopian Agricultural Business Corporation
  • Buyer's registered address: ከሳሪስ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 (ሦስት መቶ ብር)
  • Published on: Be'kur (Nov 02, 2026)
  • Posted at: 2026-11-03T13:13:32.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders