Equipment and Accessories
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለፕላንት ለማሽነር መሳሪያና ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ለ/ሴ ተ/ክ/ማ/ማ 02(001-001/2019)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለፕላንት ለማሽነር መሳሪያና ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት ቁጥር
|
የሚገዛው እቃ አገልግሎት
|
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
ሎት 1 |
ለፕላንት ለማሽነር መሳሪያና ዕቃዎች ግዥ
|
100,000.00 C.P.O.
|
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥና ፋይናንስ መመሪያዎችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ - መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢመሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
5. ድርጅቱ ያሸነፈውን ጠቅላላውን ዕቃና ግብዓት በአንድ ወር ማቅረብ የሚችል።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 100064096718 በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት እሰከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ከማዕከሉ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የሚመረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ማዕከሉ ባወጣው ስፔስፊክሽነ መሰረት ብቻ በማድረግ ቫትን ጨምሮ ሞልተው የሽገው ኤንቨሎፕ ላይ ፋይናሻልና ኦርጅናልና ኮፒ ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ቴክኒካል ብለው በአራት ፖስታ በመለየት የግዥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው መሰረት ለዚሀ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8.ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
10 ተጫራቾች አላቂ የትምህርት ግብዓት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
11. የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ብቻ ነው።
12. Greenhouse installation ስራዎችን በተመለከተ ስራውን ለመስራት የሚያስችል ሰርተፍኬት እና ከዚህ በፊት ስራውን ስለመሰራቱ የመልካም ስራ አፈጻጸም ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
ማሳሰቢያ፤ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው አካላት በተገኘበት ጨረታው ይከፈታል።
ኣድራሻ -- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የግዥ ንብረትና ህንፃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ።
ስልክ ቁጥር:-011 143 7 8666
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-11-18
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-18 10:30
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Lnegewa Setoch Rehabilitation Center
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
- Posted at: 2026-11-06T07:20:29.000Z
- Source: Qelal Tenders